1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቶጎ፤ የጀርመን የአብነት ቅኝ ግዛት

ዓርብ፣ መጋቢት 6 2016

አውሮጳውያን በምዕራብ አፍሪቃ የባህር ዳርቻዎች ለክፍለ ዘመናት የዘለቀ የንግድ እንቅስቃሴ አድርገዋል። አካባቢው በአውሮፓ ካርታ ሠሪዎች ዘንድ የባሪያ ንግድ ጠረፍ ተብሎ ይታወቅ የነበረ ሲሆን የባርነት ንግዱም እስከ 19 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ የዘለቀ ነበር።

https://p.dw.com/p/4ddKV
Teaser Shadows of german colonialism AMH
ምስል DW

 አውሮጳውያን በምዕራብ አፍሪቃ የባህር ዳርቻዎች ለክፍለ ዘመናት የዘለቀ የንግድ እንቅስቃሴ አድርገዋል። አካባቢው በአውሮፓ ካርታ ሠሪዎች ዘንድ የባሪያ ንግድ ጠረፍ ተብሎ ይታወቅ የነበረ ሲሆን  የባርነት ንግዱም እስከ 19 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ የዘለቀ ነበር።በባሪያ ንግድ ላይ ተሰማርተው የነበሩ የአካባቢው ቡድኖች በባሪያ ንግዱ ትርፋማ ነበሩ ። የጀርመን ፊውዳል ጦር አዛዥ  ጉስታቭ ናችቲጋል በ1884 ከኤው ንጉስ ምላፓ 3ኛ ጋር የሞግዚትነት ስምምነት በተፈራረሙበት ወቅት የቶጎ ልሂቃን ከተለያዩ የአውሮጳ ቅን ገዢዎች ጋር ግንኙነት ያደርጉ ስለነበር ስጋት መሆን አልቻሉም ነበር ። ከዚህ ይልቅ ግን በውስጥ የሚያደርጉት የእርስ በእርስ ግጭት እና ጦርነት ጎልቶ ይታይ ነበር ።

 ታዲያ በዚህ ጊዜ ግን፣ የጀርመን የመጀመሪያው የሞግዚትነት ግዛት ሎሜ ውስጥ የተረጋገጠ ሲሆን ፤ ብዙም ሳይቆይ የአውሮጳ ካርታ ሰሪዎች  የምዕራብ አፍሪካ የባህር ዳርቻዎችን  የብሪቲሽ ጎልድ ኮስት፣ ጀርመን ቶጎላንድ እና የፈረንሳዊ ዳሆሚ በማለት ከፋፍለው ቀርጸዋቸዋል።

 ጀርመን የቅኝ ግዛቱን በሰላማዊ መንገድ ነበር የተረከቡት ?

አይደለም ፤ ምንም እንኳ የጀርመን ምስራቅ አፍሪቃ ከሚባሉት ከዋናዋ ታንዛንያ ግዛት ፣ ቡሩንዲ እና ርዋንዳ እንዲሁም ከደቡባዊ ምዕራብ አፍሪቃ ይልቅ ቶጎ ለጀርመኖቹ ለአገዛዙ ምቹ እና ሰላማዊ እንደነበረች ቢነገርም ፤ እንደዚያ ግን አልነበረም ።

የጀርመን ፊውዳሎች የባህር ዳርቻ አካባቢዎችን ከተቆጣጠሩ በኋላ ብዙም ሳይቆዩ ወደ ማዕከላዊ የሀገሪቱ ክፍል ወታደራዊ መስፋፋት አደረጉ ። በዚህም በጎርጎርሳዊያኑ በ1884 እና 1902  መካከል ብቻ 60 ያህል የተለያዩ ወታደራዊ ዘመቻዎች መከናወናቸው ተመዝግቧል።

ቶጎ እንዴት አብነት የቅን ግዛት ተባለች?

ነገሮች ሰላም እንደሆኑ ከሚነገረው ጎን ለጎን ቶጎ ራሷን የቻለች ብቸኛ የጀርመን ቅን ግዛት ሀገር ነበረች። ነገር ግን ምንም እንኳ መመዘኛ ቢያስፈልገውም በበዝባዥ የእርሻ ስራ ላይ ለተሰማራው የጀርመኖቹ የንግድ ስራዎች ገንዘብ ማስገኘት ይጠበቅበታል።

የጀርመን ቅኝ ገዥዎች በሰው ጉልበት የሚለሙ የቡና፣ የጥጥ እና የኮኮዋ እርሻንዎችን ጨምረው  ሌሎችንም አስተዋውቀዋል። የአካባቢው ማህበረሰብ በተንጣለለው የእርሻ ማሳ ላይ በገበያ ላይ ተፈላጊ የሆኑ ምርቶችን ሲያመርቱ ጥቂት ክፍያ አልያም በነጻ እንዲሰሩ ይገደዱ ነበር። በአብዛኛው ወደ ውች ከሚላከው የግብርና ምርት የሚገኘው ትርፍ በጀርመኖች እጅ የሚገባ ሲሆን ይባስ ብሎ በጥቃቅን መሬት ላይ የሚያርሱ ትንንሽ ገበሬዎች ጭምር ለጀርመኖቹ ግብር እንዲከፍሉ ግዴታ ይጣልባቸው ነበር።  

የጀርመን ቅኝ ገዥው አስተዳደር በቶጎ ለሰራተኞች ደህንነት አልያም በሀገሪቱ መሠረተ ልማት ላይ ትንሽ መዋዕለ ንዋይ አፍስሷል። በሰብአዊ መብት አያያዝ ረገድ ግን ቶጎ እንደሌሎች የጀርመን የቅኝ ተገዢዎች ሁሉ  የከፋ መሆኑ ይነገርላታል። ስረዓቱ የከፋ ዘረኝነት፣ አካላዊ ቅጣት እና አፈና ሲፈጽም  የቅኝ ግዛት አስተዳደሩን የሚቃወሙ ግለሰቦችን ደግሞ ያሳድዳል።

የቅኝ ግዛቱ  በአካባቢ የአስተዳደር መዋቅሮች ላይ ጉዳት አድርሶ ይሆን ?

እንደ አንድ የቅኝ ግዛት የቶጎላንድ  ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ የተሰመሩ ድንበሮች የአካባቢው ነዋሪዎች የሚኖሩበት ወይም የሚገናኙበትን የገሃዱ ዓለም እውነት የሚያንጸባርቅ ሆኖ አልተገኘም።  ይህ እስከ ዛሬም ድረስ በካርታ ላይ በግልጽ ይታያል። ለአብነትም  ጋና፣ ቶጎ እና ቤኒን ከትንንሽ የባህር ዳርቻዎቻቸው ጀምሮ ወደ መሃል ሀገር የተሰመረው የካርታ ላይ ምስል ልክ እንደ ቁርጥራጭ ኬክ ያለ ቅርጽ ሰጥቶታል። 

በጥቂት የጀርመን መኮንኖች እና በውጪ የአፍሪካ ቅጥረኛ ወታደሮች ላይ ይተማመን የነበረው የወቅቱ የቅኝ ገዢው አገዛዝ  ተቃውሞን በማፈን እና  ባህላዊ የሃይል አወቃቀሮችን በታዛዥ አለቆች በመተካት ጭምር በነዋሪዎች ላይ የዘፈቀደ ጥቃት ፈጽሟል ።