1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ትግራይ፣ የሴቶች መደፈር 

ማክሰኞ፣ መጋቢት 7 2013

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር የሴቶች ቢሮ እንዳስታወቀዉ በክልሉ ርዕሰ-ከተማ መቀሌ፣ አዲግራትና አካባቢዎቻቸዉ፣ ካለፈዉ ታሕሳስ እስከ የካቲት በነበረዉ ጊዜ ብቻ ከ500 በላይ ሴቶች መደፈራቸዉ ተረጋግጧል።

https://p.dw.com/p/3qhjY
BG Tigray | Safe House
ምስል Maria Gerth-Niculescu/DW

በሁለት ከተሞችና አካባቢያቸዉ ከ500 በላይ ሴቶች ተደፍረዋል


በትግራይ ክልል በተደረገዉ ጦርነት መሐል እስካሁን ቁጥራቸዉ በዉል ያልታወቀ ግን በርካታ ሴቶች መደፈራቸዉ እየተዘገበ ነዉ። የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር የሴቶች ቢሮ እንዳስታወቀዉ በክልሉ ርዕሰ-ከተማ መቀሌ፣ አዲግራትና አካባቢዎቻቸዉ፣ ካለፈዉ ታሕሳስ እስከ የካቲት በነበረዉ ጊዜ ብቻ ከ500 በላይ ሴቶች መደፈራቸዉ ተረጋግጧል። በመግለጫዉ መሰረት አብዛኞቹ ሴቶች የተደፈሩት በኤርትራና በኢትዮጵያ ወታደሮች ነዉ።የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር የኮሚኒኬሽን ቢሮ የመላዉ ዓለም ሴቶች ድርጊቱን እንዲያወግዙና ወንጀለኞች ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቋል።

ሚሊዮን ኃይለስላሴ 

ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ