ሙዚቃ
የቴዎድሮስ ካሳሁን ቃለ-መጠይቅ በዶይቼ ቬለ
ዓርብ፣ ግንቦት 11 2009ማስታወቂያ
የሚያዜማቸዉን ሙዚቃዎች ዜማ ከግጥም ደርሶ ማቅረቡን ራሱ ይናገራል፤ አንዳንዶችም ይመሰክሩለታል። ግን ደግሞ የአባቱን ታዋቂ ገጣሚነት እየጠቀሱ የአባቱን ሥራዎች ነዉ የሚያንጎራጉረዉ የሚሉት አሉ። ቴዎድሮስ ካሳሁን ግን መልሱ አጭርና ቁርጥ ያለ ነዉ፤ «የራሴን ዜማና ግጥማ አንጎራጉራለሁ»። ታስሮም ነበር ቴዲ፤ የሙዚቃ ድግሶች (ኮንሰርቶችን) ሊያቀርብ ነዉ እየተባለም ተሰረዘ ሲባል ተሰምቷል። ቴዎድሮስ ካሣሁንን እሁድ በመዝናኛ ዝግጅታችን እንግዳ አድርገን እነዚህን ጉዳዮች አንስተንለታል።