ሳይንስ
ቴክኖሎጂ የምርጫ ስጋት ሲሆን
ረቡዕ፣ ጥቅምት 28 2011ማስታወቂያ
በአሜሪካ ከፕሬዝዳንት ምርጫ በሁዋላ ተከታትሎ በሁለተኛው ዓመት የሚካሄደው የህዝብ እንደራሴዎች ምርጫ አንድ ዓላማ አለው። እርሱም በፕሬዝዳንቱ ስራ ላይ የድጋፍ ወይም ደግሞ ይህን ሰው መቆጣጠር አለብን የሚል የተቃውሞ ማስጠንቀቂያ ያዘለ ነው። ፖለቲከኞች በስልጣናቸው እንዳይባልጉ የመቆጣጠርም ልጓምም ነው። ዘንድሮ ከዚሁ ጋር ሌላው ችግር ህዝቡ የሰጠው ድምጽ በትክክል ተቆጥሯል ወይስ ባልሆነ ምክንያት ተጨብርብሯል የሚል ነው።
የዕለቱ የሳይንስና ቴክኖሎጂ መሰናዷችን የ21ኛውን ክፍለ ዘመን የዲሞክራሲ ስርዓት ጋሬጣ ነው ስለሚባለው ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ የምርጫ ውጤቶችን መዛባት ጉዳይ ይዳስሳል። ሙሉ መሰናዶውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።
ይልማ ኃይለሚካኤል
ተስፋለም ወልደየስ