ታሪካዊው የአየር ንብረት ለዉጥ ስምምነት
ሰኞ፣ ታኅሣሥ 4 2008ማስታወቂያ
195 ሀገራት ያጸደቁትን ይህንኑ የፓሪስ ስምምነት የጀርመኗ መራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የአየር ንብረት ለውጥን ለመግታት ቁርጠኝነቱን ያሳየበት ነበር» ብለውታል። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ ባን ኪ ሙን እንዲሁም የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርሲያን ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ሳይቀሩ ስምምነቱን አወድሰዋል። ጉባዔው እንደ ቻይና እና ሌሎች በርካታ ሀገራት በመሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ባለመግባባታቸው ለአንድ ቀን መገፋቱ ይታወሳል። አሁን ሀገራቱን መልሶ ስላስማማው ስለዚሁ የጉባዔ ውጤት እና ቀጣይ ርምጃ ብራስልስ የሚገኘው ወኪላችን ገበያው ንጉሴን ጠይቀንዋል።
ገበያው ንጉሴ
ልደት አበበ
አዜብ ታደሰ