1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ተቃውሞ በትግራይ ክልል 

ማክሰኞ፣ ግንቦት 18 2012

በክልሉ አስገደ ወረዳ ማይ ሓንሰ ነዋሪዎች በዚሁ ቅሬታ ከአካባቢያቸው ወደ ሽረ የሚወስደውን መንገድ ዘግተዋል፡፡በዋጅራትም የወረዳው ማዕከል ወደ ሌላ አካባቢ ተወስዷል የሚል ቅሬታ ያላቸው ነዋሪዎች በሰልፍ ተቃውሞአቸውን ገልጸዋል።ለጥያቄዎቹና ተቃውሞዎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የወረዳዎቹ ባለሥልጣናት መልስ ለማግኘት ዶቼቬለ ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።

https://p.dw.com/p/3cn4S
Äthiopien Stadtansicht Mekele
ምስል DW/M. Hailessilasie

ተቃውሞ በትግራይ ክልል

በትግራይ ክልል ወጀራትና አስገደ ወረዳዎች እንደ አዲስ ከተደራጁ ወረዳዎች ማዕከልነት ጋር በተያያዘ ነዋሪዎች ተቃውሞአቸውን እየገለፁ ነው፡፡ በክልሉ አስገደ ወረዳ ማይ ሓንሰ ነዋሪዎች በዚሁ ቅሬታ ከአካባቢያቸው ወደ ሽረ የሚወስደውን መንገድ ዘግተዋል፡፡በወጀራትም የወረዳው ማዕከል ወደ ሌላ አካባቢ  ተወስዷል የሚል ቅሬታ ያላቸው ነዋሪዎች እሁድ በሰልፍ ተቃውሞአቸውን  ገልጸዋል። ዶቼቬለ ለነዚህ ጥያቄዎችና ተቃውሞዎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የወረዳዎቹ ባለሥልጣናት መልስ ለማግኘት  ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።ዝርዝሩን ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ ከመቀሌ ልኮልናል።
ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ 
ኂሩት  መለሰ
ነጋሽ መሐመድ