ባራክ ኦባማ በአውሮጳ
ሰኞ፣ መጋቢት 21 2001ማስታወቂያ
ብሪታንያ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ የቼክ ሬፑብሊክ እና ቱርክ፤ የየዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ከነገ ጀምሮ የሚጎበኟቸው የአውሮጳ ሀገሮች ይሆናሉ። የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት ዋና ዓላማም፤ በለንደን በሚካሄደው የቡድን ሃያ ጉባኤ እንዲሁም በሽትራውስበርግ እና በኬህል ከተሞች በሚከናወነው የሰሜን አትላንቲክ ቃል-ኪዳን ድርጅት ስብሰባ ላይ ለመካፈል እንደሆነም ታውቋል። ከወዲሁ የአውሮጳ ሕዝብና ፖለቲከኞች የፕሬዚዳንቱን ጉብኝት በከፍተኛ ጉጉት እየጠበቁት ነው። በተለይ የአውሮጳ ፖለቲከኞች ኦባማ በርግጥም የሚስማሟቸው ስለመሆኑ ከጉብኝቱ ማረጋገጥ ይፈልጋሉ። ሆኖም አንዳንድ ተንታኞች ያን ያህል በከፍተኛው መጠበቅ እንደማይገባ እያስጠነቀቁ ነው።
ማንተጋፍቶት ስለሺ