ባልደራስ የመጀመርያውን ጉባኤ አካሄደ
ሰኞ፣ የካቲት 2 2012ማስታወቂያ
ቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ በፍትሃዊና ታማኝነት እንዲከናወን የአውሮፓ ሕብረት ታዛቢዎች ገብተው እንዲከታተሉ ግፊት አደርጋለሁ ሲል ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ገለጸ። ፓርቲው ትናንት የመጀመሪያ መስራች ጉባኤዉን ያከናወነ ሲሆን 60 የፓርቲው አመራሮችንና የብሄራዊ ምክር ቤት አባላትን ስም ለጉባኤተኛው አስተዋውቋል። ጉባኤውን በመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ጽ/ቤት ያደረገው ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ጉባኤውን ሌላ ቦታ እንዳያደርግ በከተማ አስተዳድሩ ክልከላ ተደርጎበታል በማለት የፓርቲው ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡት አቶ እስክንድር ነጋ ተናግረዋል።
ሰለሞን ሙጬ
ታምራት ዲንሳ
ሸዋዬ ለገሠ