ቢንያም ዳና እና « የኛ ስታይል»
ዓርብ፣ ነሐሴ 3 2005ማስታወቂያ
ትልቁ የኢንተርኔርት የቪዲዮ ማህደር YOU TUBE ላይ ብዙ « ላይክ» ወይንም ተወዳጅነት ያገኘ ቪዲዮ በመባል ጋንግናም ስታይል እኢአ በመስከረም ወር 2012 ዓ ም የጊነስ የዓለም ክብረ ወሰን መዝገብ ላይ ሰፍሯል። በታህሳስ ወርም ዮቲውብ ላይ ቢሊዮን ጊዜ የታየ የመጀመሪያው ቪዲዮ ተብሏል። ዛሬ ገፁ ከ 1,7 ቢሊዮን በላይ ተጎብኝቷል። ቢንያም ዳና የተጫወተው « የኛ ስታይል» ደግሞ ይፋ ከሆነ ሁለት ወር ሊሆነው ነው ይላል። ወደ ኪነ ጥበብ ሙያ ከገባው 16 ዓመት ሊሞላኝ ነው ይላል ቢንያም።
እሱ እንደሚለው ይህንን ቪዲዮ አይተው ሰዎች የሰጡት አስተያየት ይበልጥ ሙዚቃ እንዲጫወት አበረታትቶታል። ቢንያም በደቡብ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የመድረክ መሪ ሆኖ ይሰራል። ሙዚቃ በትርፍ ጊዜ ነው የሚጫወተው።
በህዝብ ዘንድ « የኛ ስታይል» ምን አይነት አቀባለል አገኘ ? ይህንን ዘፈንስ ለመጫወት ምን አነሳሳው፤ ቢንያም አጫውቶናል።ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።
ልደት አበበ
ሸዋዬ ለገሰ