በወግ ያልተያዘዉ ሀብት
ማክሰኞ፣ ጥር 28 2005ማስታወቂያ
ከተፈጥሮና የአጠቃቀም ጉድለት ተዳምሮም ሐይቆችና ወንዞችን ማድረቅ መጀመሩም የዚህ ማስጠንቀቂያ ነዉ የሚሉ አሉ። መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ወንዞች እና ሃይቆች ዉሃቸዉ ነጥፎ እየደረቁ ነዉ። ሰባት ቢሊዮን ለደረሰዉ የዓለም ህዝብ መሠረታዊ የሆነዉ ህይወት አለምላሚ ዉሃ ከየምንጩ በሚያርፍበት ከፍተኛ የተፈጥሮና ሰዉ ሠራሽ ምክንያት ለችግር መጋለጡ ይታያል።
ዉሃ ለመጠጥ፤ እህል ለማምረት፤ ምግብ ለማብሰል፤ ለኃይል ምንጭነት እንዲሁም ለኢንዱስትሪ ምርትና ለመሳሰሉት በከፍተኛ ደረጃ ሥራ ላይ ይዉላል። በየቀኑ ለእርሻ፤ ለኢንዱስትራና ለንግዱ ዘርፍ የሚዉለዉ ሳይጠቀስ አራት የቤተሰብ አባላት በአንድ ቤት ብቻ በአማካኝ ወደ400 ጋሎን ዉሃ ይጠቀማሉ ተብሎ ይገመታል። የዉሃዉ ምንጭ ጥንቃቄ ስለማይደረግለትም ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ ሀገሮች የዉሃ አካላት መድረቃቸዉ እየታየ ነዉ። ጥናቶች ከወዲሁ እንደሚያመለክቱት እንደልብ ያለዋጋ በየወንዙና ባህሩ የሚፈሰዉ ዉሃ ከዓመታት በኋላ እንደተፈለገ ሊገኙ ከማይችሉ የተፈጥሮ ሃብቶች ተርታ ሊገባ እንደሚችል ነዉ።
ሸዋዬ ለገሠ
ተክሌ የኋላ