በወልቂጤ ከተማ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጣለ
ሰኞ፣ ጥቅምት 5 2016የጉራጌ ዞን መስተዳድር በወልቂጤ ከተማ የሰውና የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ገደብ ጣለ ፡፡ የአንቅስቃሴ ገደቡ የተጣለው በጉራጌ እና በቀቤና ብሄር አባላት መካከል በተነሳው ግጭት ሁለት ሰዎች ተገድለው ሌሎች አሥራ ስድስት መቁሰላቸውንና ንብረት መዘራረፋቸውን ተከትሎ ነው፡፡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በበኩሉ በከተማው በሰውና በንብረት ላይ ሊደርስ የሚችለውን ተጨማሪ ጉዳት ለማስቀረት በሚል ከቅዳሜ ጀምሮ በሰዎችና በተሽከርካሪ እንቅስቃሴዎች ላይ ገደብ እንደጣለ ይገኛል ፡፡ወልቂጤን ጨምሮ በጉራጌ ዞን ከተሞች የሥራ ማቆም አድማ
መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ግጭቱ የተነሳው ከባለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ነው፡፡ ግጭቱ የተቀሰቀሰው የቀቤና ልዩ ወረዳ አደራጀጀትን በሚደግፉ የቀቤና ወጣቶችና መዋቅሩን በሚቃወሙ የጉራጌ ወጣቶች መካከል በተከሰተ መጠቃቃት መሆኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል ፡፡ በሁለቱ ብሄር አባላት መካከል ተከሰተ በተባለው ግጭት በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን በአካባቢው ነበርን ያሉ የአይን አማኞች ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል፡፡በጉራጌ ዞን ጉንችሬ ግጭት ሰውና ንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ
የአሁኑ ግጭት የተከሰተው ቀደምሲል በጉራጌ ዞን ሥር ሲተዳደር የቆየው የቀቤና ወረዳ በአዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ራሱን በቻለ የልዩ ወረዳ አስተዳደር ለመዋቀር የሚበቃውን መሥራች ጉባዔውን ማካሄዱን ተከትሎ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል ፡፡ “ ልዩ ወረዳው ተጠሪነቱ ከጉራጌ ዞን መስተዳድር ሥር ከወጣ መቀመጫውን ከወልቂጤ ከተማ ውጪ ማድረግ ይኖርበታል “ የሚሉ ወጣቶች በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅስቀሳ ሲያደርጉ መቆየታቸውን አስተያየት ሰጪዎቹ ተናግረዋል ፡፡ የልዩ ወረዳው የአደረጃጀት ጉዳዩ ሲብላላ ቆይቶ የሁለት ወጣቶችን የግል ጸብ ምክንያት አድርጎ ሊቀሰቀስ መቻሉን ነው ነዋሪዎቹ የጠቀሱት ፡፡
ዶቼ ቬለ የጉራጌን ዞንና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሥራ ሃላፊዎች የጉራጌ ተወላጆች «ምሥራቅ ጉራጌ ዞን » የተባለ አዲስ የዞን አስተዳደር እንዲዋቀርላቸው በሰላማዊ ሰልፍ ጠየቁበጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጡ ቢጠይቅም ከተማው በጥምር ወታደራዊ ዕዝ ወይም ኮማንድ ፖሰት የሚመራ በመሆኑ የተናጠል አስተያየት ለመስጠት እንደሚቸግሩ ገልጸዋል ፡፡
ያምሆኖ የከተማው አስተዳደር በከተማው የሚታየው አለመረጋጋት የተነሳ በሰውና በንብረት ላይ ሊደርስ የሚችለውን ተጨማሪ ጉዳት ለመቀነስ በሚል ከቅዳሜ ጀምሮ በሰዎችና በተሽከርካሪ እንቅስቃሴዎች ላይ ገደብ መጣሉን አስታውቋል ፡፡
የሞተር ሳይክሎች፣ ባለሦስት እግር ተሽከርካሪ ባጃጆች፣ አነስተኛና ከፍተኛ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎችና ነዋሪዎች ከቀኑ11:00 እስከ ጠዋት 1:00 ድረስ እንቅስቃሴ ማድረግ የተከለከለ መሆኑን ዞኑ በመግለጫው ዘርዝሯል፡፡በመስቃን እና በማረቆ ማህበረሰብ መካከል የተቀሰቀሰ ግጭት
የአንቅስቃሴ ገደብ መጣሉን ተከትሎ ዛሬ ሰኞ የተወሰነ የጥይት ድምፅ ከመሰማቱና አገልግሎት መስጫዎች ከመዘጋታቸው በስተቀር አንጻራዊ ሰላም መኖሩን አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል ፡፡
ፎቶ ከወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን የተወሰደ
ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ታምራት ዲንሳ
አዜብ ታደሰ