1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኦሮሚያ የአንበጣ መንጋ ወረርሽኝ ሰብል ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 3 2013

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሐረርጌ የበረሃ አንበጣ ወረርሽኝ ምርታቸውን ከጥቅም ውጭ እያደረገባቸው መሆኑን አርሶአደሮች ተናገሩ፡፡ በዞኑ የጭሮ ወረዳ አርሶ አደሮች እንደተናገሩት ከምንገዜውም የከፋ የአንበጣ መንጋ አጋጥሞአቸዋል።

https://p.dw.com/p/3jrk2
Heuschreckenangriff in den Wohngebieten von Jaipur, Rajasthan
ምስል picture-alliance/NurPhoto/V. Bhatnagar

የአንበጣ መንጋዉ ዘንድሮ በአራት እጥፍ ጨምሮአል


በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሐረርጌ የበረሃ አንበጣ ወረርሽኝ ምርታቸውን ከጥቅም ውጭ እያደረገባቸው መሆኑን አርሶአደሮች ተናገሩ፡፡ በዞኑ ጭሮ ወረዳ የነጀባስ እና ጭሮ ቀላ ቀበለያት አርሶ አደሮች ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት ከምንገዜውም የከፋ የአንበጣ መንጋት አጋጥሞአቸዋል። አርሶአደሮቹ ከሰብላቸው ለዘር እንኳ የሚሆን ምርት ለማግኘታቸው እንደሚጠራጠሩ ነው የገለጹት፡፡ በዞኑ የጭሮ ወረዳ ግብርና ጽ/ ቤት አንዳለው በጭሮ ወረዳ ከሚገኙ 38 ቀበሌዎች 26 ቱ በአንበጣው መንጋ ክፉኛ ተጎድተዋል፡፡ በምዕራብ ሃራርጌ 8 ወረዳዎች 163 ቀበሌዎች የአንበጣ መንጋው ጉዳት ማድረሱን ደግሞ ከዞኑ አደጋ ስጋት አመራር ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡

ስዩም ጌቱ

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሰ