በእየሩሳሌም ሙክራብ ላይ የደረሰ ጥቃት
ማክሰኞ፣ ኅዳር 9 2007ጥቃት አድራሾቹ ዕድሜያቸው በ20ቹ መጀመሪያ ላይ የሚገኝ ፍልስጤማውያን ናቸው ተብሏል። ምስራቅ እየሩሳሌም ውስጥ ከሚገኝ ጃበል ሙካበር ከተባለ ከተማ። ቢሊዋ ፣ መጥረቢያ እና ጠመንጃ ተጠቅመው ነው ሁለቱ ወጣቶች በአይሁዶች ቤተ መቅደስ ላይ ደም ያፋሰሱት። ወጣቶቹ ከፖሊስ በተከፈተ ተኩስ ተገድለዋል። ከዚህ ጥቃት በኋላ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔትናያሁ እስራኤል ጠንከር ያለ ርምጃ እንደምትወስድ አስታውቀዋል። ወጣቶቹ ጥቃቱን ለምን አደረሱ ስለሚለው ብዙም የሚጠይቅ የለም። የምጣኔ ሀብት ሚኒስትር ቤኔት ለዚህ ሁሉ ተጠያቂ የሚያደርጉት ፤ አሸባሪ ብለው የሚጠሯቸውን የፍልስጤም ፕሬዚዳንት አባስ ነው።«በምናባዊዉ የመካከለኛዉ ምሥራቅ ዲፕሎማሲ ጉዳይ በተያዝንበት ወቅት ፍልስጤማዉያን በሽብርና በማነሳሳት ከበዉናል። በተቃራኒዉ ግን ሽብር እንቅፋት ነዉ የሚያስከትለዉ። አባስ እስራኤል ላይ ጦርነት አዉጀዋል፤ እናም አፀፋዉን በተገቢዉ መንገድ መመለስ አለብን።»
የቀድሞው የእየሩሳሌም የፖሊስ አዛዥ አሪ አሚትም ቢሆኑ መፍትሄው ጦርነት ነው ሲሉ ነው በእስራኤል ራዲዮ ዛሬ የተሰሙት።« ጠማንጃ ያለው ሰው ሁሉ ኪሱ ይሸጉጥ፣ የጦር መሳሪያ ፍቃዱን ደግሞ የገንዘብ ቦርሳው ውስጥ ይክተት። ፍርድ ቤት ችግር እንጋይገጥመው ማለት ነው። ያለነው ጦርነት ውስጥ ነው ስለዚህ ጦርነት ውስጥ እንዳለን አውቀን መንቀሳቀስ ይኖርበናል። ሁላችሁም ሽጉጣችሁን ይዛችሁ ፖሊሶችን ደግፉ።»
ስልጣን ላይ ያሉት የፖሊስ አዛዥ ጆሀናን ዳኒኖ ግን መረጋጋትን ነው የሚጠይቁት።« ያለው ቁጭት ይገባኛል። ህመሙንም እረዳለሁ። በግልፅ ግን መናገር የምፈልገው። ስራችንን እንድንፈፅም ለኛ ተዉልን። ህጉ የማይፈቅደውን ነገር ለማድረግ አትሞክሩ። ጥቃት ለመጣል የሚያስቡት ላይ አግባብ የሆነውን ርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ነን። ሁላችንም ግን አሁን መረጋጋት ይኖርብናል።»
ፖሊስ እና የሀገሩቱ የስለላ ድርጅት አደጋው የደረሰበት ቦታ ተገኝቶ ምርመራ አካሂዷል። ከዚህም በተጨማሪ የጥቃት ጣዮቹን ወላጆች በቁጥጥር ስር አውለዋል።
ክርስቲያን ቫግነር / ልደት አበበ
ተክሌ የኋላ