በኤርትራ ላይ እንዲጣል የታሰበው እገዳ
ሰኞ፣ ጥቅምት 13 2004ማስታወቂያ
አዲሱ ረቂቅ ማዕቀብ በኤርትራ፣ የማዕድን ኢንዱስትሪና፣ አገሪቱ ፤ በውጭ ከሚገኙ ዜጎቿ በምታገኘው የግብር ገቢ ላይ ያነጣጠረ ነው ። ምክር ቤቱ ባለፈው ሳምንት የተወያየበትን ረቂቅ ህገ ደንብ ያቀረበችው ጋቦን ስትሆን ፣ ናይጀሪያም ማዕቀቡን ደግፋለች ። ይሁንና ረቂቁ ድምፅ እንዲሰጥበት ወደ ምክር ቤቱ ገና አልተመራም ። ረቂቁ ቢፀድቅ በኤርትራ ላይ ብርቱ ችግር የሚያስከትል መሆኑ አያጠራጥርም ። ዝርዝሩን ፤ አበበ ፈለቀ ልኮልናል ፤
አበበ ፈለቀ
ሂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ