በብሪታንያ የሚኖሩ ኤርትራዉያን አስተያየት
ሰኞ፣ ሐምሌ 2 2010ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ህዝብ በሃገራቱ ሰላም መስፈኑ አስመራ ላይ የተዉለበለበዉ የሰላም ዘንባባ ፤ እናቶች በእልልታ፤ ወጣቱ ሆታ፤ የሁለቱን ሃገሮች ሰንደቃላማ እያዉለበለበ እያዜመ የኢትዮጵያዉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በሞቀ ድግስ መቀበሉ ለሰላም እና ለፍቅር ያለዉን ፍላጎት በጉልህ ያሳየ ነዉ። በሁለቱ ሃገራ ይህ አይነት ሰላም መንገሱ የሁለቱን ሃገራት ብቻ ሳይሆን ለቀጠናዉ፤ ብቻ ሳይሆን በዓለም ያለዉን ሰላም ፈላጊ ማኅበረሰብ ያስፈነደቀ መሆኑን ኤርትራዉያኑ ገልፀዋል። የለንደኑ ወኪላችን በለንደን ነዋሪ የሆኑ ኤርትራዉያንን ስለ ኢትዮ ኤርትራ አዲስ ግንኙነት አስተያየታቸውን ጠይቆ አጠር ያለ ጠገባ ልኮልናል።
ድልነሳህ ጌታነህ
አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ