1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሰሞኑን በአማራ ክልል የተካሄዱ ህዝባዊ ዉይይቶች ላይ የተሰጡ አስተያየቶች

ማክሰኞ፣ ጥር 28 2016

በአማራ ክልል የተፈጠረውን የሰላም መደፍረስ በዘላቂነት ለመፍታትና አሉ በተባሉ ችግሮች ዙሪያ የፌደራልና የሁሉም ክልሎች ከፍተኛ ኃላፊዎች ሰሞኑን በአማራ ክልል 15 ያህል ከተሞች ህዝባዊ ውይይት አድርገዋል፡፡ ነዋሪዎች ውይይቱን በአወንታዊ ሲመለከቱት ሌሎች ደግሞ ውይይቶቹ ማዘናጊያና ሲሉ ተችተዋል፡፡

https://p.dw.com/p/4c65y
ባህር ዳር ከተማ፤ የአማራ ክልል መዲና
ባህር ዳር ከተማ፤ የአማራ ክልል መዲናምስል Alemnew Mekonnen/DW

በአማራ ክልል የተካሄዱ ህዝባዊ ዉይይቶችን አንዳንድ የክልሉ ነዋሪዎች በአወንታዊ ሌሎች ደግሞ ማዘናጊያና ብለተዋል፡፡

በአማራ ክልል የተፈጠረውን የሰላም መደፍረስ በዘላቂነት ለመፍታትና  አሉ በተባሉ ችግሮች ዙሪያ የፌደራልና የሁሉም ክልሎች ከፍተኛ ኃላፊዎች ሰሞኑን በአማራ ክልል 15 ያህል ከተሞች  ህዝባዊ ውይይት አድርገዋል፡፡

በሕዝባዊ ውይይቱ በክልሉ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ አስቸጋሪ ስለመሆኑ፣ የማንነትና የወሰን ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ ማግኘት አለመቻላቸው፣ የህገ መንግስት ይሻሻል ጥያቄ በወቅቱ መፍትሔ አለማግኘቱና የተፈናቃዮች ሁኔታና ሌሎችም “ገፊ” የተባሉ ችግሮች በክልሉ ለተፈጠረው የሰላም መደፍረስ ምክንያት እንደሆኑ በስፋት ተነስተዋል፡፡

ባለስልጣናቱ ማንኛውም ጥያቄ አለኝ የሚል አካልና በተወያዮቹ ለተነሱ ጥያቄዎች መንግስት ለመወያየትና ችግሮቹ አንዲፈቱ በሩ ክፍት መሆኑን አመልክተዋል፡፡ በውይይቱ ዙሪያ ያነጋገርናቸው አንዳንድ የክልሉ ነዋሪዎች ውይይቱን በአወንታዊ ሲመለከቱት ሌሎች ደግሞ ውይይቶቹ ማዘናጊያና በህዝብ ያልተወከሉ ሰዎች የተሳተፉባቸው መድረኮ ናቸው ሲሉ ተችተዋል፡፡

ዓለምነው መኮንን

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ