የነብርጋዴር ጄነራል ጠና ቁርንዴ ጉዳይ
ዓርብ፣ ታኅሣሥ 5 2011ማስታወቂያ
የፌድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት በነ ብርጋዴር ጄነራል ጠና ቁርንዴ መዝገብ በሙስና የተጠረጠሩ 26 ሰዎች ፖሊስ ያቀረበውን የተጨማሪ 14 ቀናት የምርመራ ጊዜ መቃወሚያ ሲያዳምጥ ውሏል። በክስ መዝገቡ ከ9ኛ እስከ 26ኛ የተዘረዘሩ ተጠርጣሪዎች በግላቸው እና በራሳቸው የፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ኢ-ምክንያታዊ እና ሕግን የሚፃረር በማለት በዋስትና እንዲለቀቁ ጠይቀዋል። ችሎቱን የተከታተለው ዝርዝር ዘገባ አድርሶናል።
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር
አዜብ ታደሰ
እሸቴ በቀለ