በቢሾፍቱ የሞቱት ጉዳይ
ረቡዕ፣ መስከረም 25 2009ማስታወቂያ
ባለፈው እሁድ በቢሸፍቱ በእሬቻ በዓል የሞቱት ሰዎች ጉዳይ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ ሽትራስቡርግ ፈረንሳይ በመካሄድ ላይ ባለው የአውሮጳ ፓርላማ መደበኛ ጉባኤ ላይ ተጠየቀ ። ጥያቄውን ያቀረቡት በ 1997 የተካሄደው የኢትዮጵያ ምርጫ የአውሮጳ ህብረት ታዛቢ እና በአውሮጳ ፓርላማ የፖርቱጋል ሶሻሊስት ፓርቲ ተወካይ አና ጎሜሽ ናቸው ። ትናንት በጉባኤው ሂደት ጣልቃ በመግባት ጥያቄውን ያቀረቡት ጎሜሽ የአውሮጳ ህብረት በኢትዮጵያ የሚፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በዝምታ ከማለፍ እንዲቆጠብም አሳስበዋል ። የብራሰልሱ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሴ ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ገበያው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ