በስደተኞች የተነሳ ጣሊያን ያላት ስጋት
ማክሰኞ፣ ግንቦት 2 2003ማስታወቂያ
ጣሊያን የሌሎች የአውሮፓ አገሮችን እርዳታም እየጠየቀች ነው። በሌላ በኩል ደግሞ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት፤ በምጻሩ NATO ከዚህ ቀደም ከሊቢያ በግጭቱ ምክንያት በርካታ ስደተኞችን አሳፍራ ወደ ላምፔዱዛ ስታመራ አደጋ የደረሰባትን መርከብ ጉዳይ ማጣራት እንደሚጀምር አስታውቋል። ጣሊያን በርካታ ስደተኞች ወደ ግዛቷ ሊመጡ እንደሚችሉ ስጋቷን እያሰማች ነው። ከማግሬብ አገሮች ብቻ ከ 300 ሺህ እስከ 400 ሺህ ሰዎች ከመኖሪያቸው መፈናቀላቸውን የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚንስትቴር ገልጽዋል።
ልደት አበበ
ነጋሽ መሐመድ