1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
እምነትኢትዮጵያ

በስልጤ ዞን በተቀሰሰ ግጭት የአንድ ሰው ሕይወት አለፈ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 30 2015

በሥልጤ ዞን ቅበት ከተማ በወጣቶችና በፀጥታ አባላት መካከል በተከሰተ ግጭት የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ ሌሎች አራት ቆሰሉ ፡፡ ለግጭቱ መቀስቀስ «መተት» ምክንያት ሆኗል። መተት ለማባረር ቀደ ጎዳና ወጡ የተባሉ ወጣቶች ከጸጥታ ኃይሎች ጋር ተጋጭተዋል፤ ወደ አዲስ አበባ የሚወስደው ዋናው አውራ ጎዳናም ተዘግቷል።

https://p.dw.com/p/4Vz4q
በከተማይቱ ትናንት አመሻሽ ላይ የተከሰተው ግጭት እና አለመረጋጋት አስከ ዛሬ አኩለ ቀን ድረስ የዘለቀ ነበር ይላሉ የከተማይቱ ነዋሪዎች  ፡፡
በስልጤ ዞን በነዋሪዎች እና የጸጥታ ኃይሎች መካከል የተቀሰቀሰ ግጭት ለሰው ህይወት መጥፋት ምክንያት ሆኗል።ምስል Silte Zone Government Communication Affairs

በስልጤ ዞን በነዋሪዎች እና የጸጥታ ኃይሎች መካከል የተቀሰቀሰ ግጭት የሰው ሕይወት አለፈ

በሥልጤ ዞን ቅበት ከተማ ምን ተፈጠረ ?   

በሥልጤ ዞን ቅበት ከተማ በወጣቶችና በፀጥታ አባላት መካከል በተከሰተ ግጭት የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ ሌሎች አራት ቆሰሉ ፡፡ግጭቱ ሊከሰት የቻለው በነዋሪዎች ላይ አድሯል ያሉትን የመተት መንፈስ ለማባረር ወደ ጎዳና የወጡ ወጣቶች  ከፀጥታ አባላት ጋር በመጋጨታቸው ነው ተብሏል ፡፡

በከተማይቱ ትናንት አመሻሽ ላይ የተከሰተው ግጭት እና አለመረጋጋት አስከ ዛሬ አኩለ ቀን ድረስ የዘለቀ ነበር ይላሉ የከተማይቱ ነዋሪዎች  ፡፡ ግጭቱ የተከሰተው በከተማው የእስልምና እምነት ተከታይ የሆኑ ወጣቶችና በዞኑ የፀጥታ አባላት መካከል መሆኑን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል ፡፡ በስልጤ የተጀመረው የሐይማኖት ተቋማት መልሶ ግንባታየግጭቱ መንስኤ በከተማው በቁጥር በርከት ያሉ ሴቶች መታመማቸውና የህመማቸው ምክንያትም “ መተት ተደርጎባቸው ነው “ የሚል መረጃ መሠራጨቱን ተከትሎ  ነው ይላሉ ዶቼ ቬለ DW  የነጋገራቸው የከተማይቱ ነዋሪዎች ፡፡

ታመዋል የተባሉ ሴቶች ተደረገባቸው የተባለውን መተት ለማስለቀቅ በከተማው የተለያዩ ጎዳናዎች ላይ  ሞንታርቦ በተባለ የድምጽ ማጉያ ቁራን ተከፍቶ እንዲሰማ መደረጉን የጠቀሱት የአይን አማኞቹ “  ይሁንእንጂ በሥፍራው የደረሱ የዞኑ የፀጥታ አባላት ሞንታርቦዎቹ እንዲነሱ ማድረጋቸውን ተከትሎ ከወጣቶቹ ጋር አለመግባባት ተፈጠር ፡፡ በዚህም ከፀጥታ አባላቱ በተተኮሰ ጥይት የአንድ ሠው ሕይወት ሲያልፍ ሌሎች አራት ደግሞ የመቁሰል ጉዳት ደርሶባቸዋል “  ብለዋል ፡፡በስልጤ ዞን የአብያተ ክርስትያናት መቃጠል

በከተማይቱ የደረሰውን ጉዳት ተከትሎ ወጣቶቹ መንገዶችን በድንጋይና በግንድ መዝጋታቸውን የአይን አማኞቹ ገልጸዋል ፡፡ በተለይም አዲስ አበባን ከሆሳዕና ፣ ከዎላይታ ሶዶ እና ከአርባ ምንጭ ከተሞች የሚገናኘው ዋና መንገድ ከትናንት ምሽት ጀምሮ ከተዘጋ በኋላ ዛሬ አኩለ ቀን አካባቢ መከፈቱንም ተናግረዋል ፡፡ በፀጥታ አባላቱ በተተኮሰ ጥይት ሕይወቱ ያለፈው አቡድልፈታህ ሙዴ የተባለው ወጣት የቀብር ሥረዓት ዛሬ ከቀትር በኋላ መፈጸሙን ጠቅሰዋል ፡፡ በግጭቱ የቆሰሉ ሌሎች አራት ወጣቶች ደግሞ በወራቤ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡ሳዑዲ የሚኖሩ የስልጤ ብሔረሰብ ሽምግልና

ዶቼ ቬለ DW  በቅበት ከተማ በተፈጠረው ግጭት ዙሪያ በየደረጃው የሚገኙ የሥራ ሃላፊዎችንና የስልጢ ወረዳ የእስልም ጉዳዮች ምክር ቤት አመራሮችን በማነጋገር ተጨማሪ መረጃ ለማሰባሰብ ያደረገው ጥረት ሃላፊዎቹ ምላሽ ለመስጠት ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ሊሳካ  አልቻለም ፡፡

ሸዋንግዛው ወጋየሁ

ታምራት ዲንሳ

ኂሩት መለሰ