በሴቶች ግርዘት ላይ የጀርመን አቋም29 ጥር 2001ዓርብ፣ ጥር 29 2001በጀርመን ህግ መሰረት ሴት ልጁን የሚያስገርዝ እስከ አስር ዓመት በሚደርስ ዕስራት ይቀጣል ።https://p.dw.com/p/Gomrምስል picture-alliance/ dpaማስታወቂያበጀርመን ህግ ላይ እንደሰፈረው የሴት ልጅን የመዋለጃ አካል መቁረጥ ማለት በጤናማ አካል ላይ አደጋ ማድረስ ነው ተብሎ ነው የሚታሰበው ። ከሴት ልጅ የመዋላጃ አካላት መቁረጥ ጋር የተያያዙ በርካታ አቤቱታዎች ጀርመን ፍርድ ቤቶች ይቀርባሉ ። ሆኖም ሁሉም ከበቂ ማስረጃ ጋር አልቀረቡም ። በዚህ የተነሳም ዳኞች ማን ድርጊቱን እንደፈፀመ እና ማን እንዳስፈፀመ ማረጋገጥ አልቻሉም ።