የርዮ ኦሎምፒክ እና ኢትዮጵያ
ረቡዕ፣ ነሐሴ 11 2008ማስታወቂያ
በሪዮ ኦሊምፒክ ትናንት ሌሊት በተካሄደው የ1,500 ሜትር የሴቶች ሩጫ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ገንዘቤ ዲባባ ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳልያ አግኝታለች። ገንዘቤ ወደፊት በ1,500 ሜትር ሩጫ የመወዳደር እቅድ እንደሌላት ተናግራ በ5,000 ሜትር ሩጫ ግን ክብረ ወሰኑን ለመስበር ግን ሙከራ እንደምታደርግ አስታውቃለች በዛሬው ዕለት በሁለት ምድብ በተካሄደው የ5,000 ሜትር የወንዶች ሩጫ የማጣሪያ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ደጀን ገብረመሥቀል፣ ሐጎስ ገብረሕይወት እና ሙክታር ኢድሪስ አልፈዋል ። የፍፃሜው ውድድሩ የፊታችን ቅዳሜ ይደረጋል።ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሚቀጥሉት ቀናት የሚሳተፉባቸው ቀሪ ውድድሮች አሉ ። በነዚህ ውድድሮችም ተጨማሪ ሜዳልያዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ። ከውድድሮቹ ምን ይጠበቃል በእስካሁኑ ውድድር የተገኙት ውጤቶችስ እንዴት ይታያሉ?የለንደንዋን ዘጋቢያችንን ሃና ደምሴን ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬያታለሁ ።
ሃና ደምሴ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ