በሪያድና በካይሮ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ተቃውሞ
ዓርብ፣ ሐምሌ 13 2004ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንግሥት ህገመንግሥቱን እንዲያከብርና በሃይምኖትም ጣልቃ እንዳይገባ በሪያድና ካይሮ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞ ምዕመናን ጠየቁ ።በነዚህ ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የሙስሊሞች ጥያቄ ይዘው ከመንግሥት ጋራ ይደራደሩ በነበሩት የኮሚቴ አባላት ላይ የተወሰደውን እርምጃና በመንግሥት መገናኛ ብዙሃን የሚካሄደውን የስም ማጥፋት ዘመቻ ተቃውመዋል ። የሪያዶቹ ኢትዮጵያውያን ተቃውሞአቸውን በስብሰባ ሲገልጹ የካይሮዎቹ ደግሞ በካይሮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ማሳመታቸውን የጅዳው ወኪላችን ነብዩ ሲራክ ዘግቧል ።
ነቢዩ ሲራክ
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ