በሣዑዲ ዓረቢያ እንደ «ግሪን ካርድ» አይነት ፈቃድ
ማክሰኞ፣ ግንቦት 6 2011ማስታወቂያ
የውጭ ሃገራት ነዋሪዎችን እንደሚመለከተው አዲሱ የሣዑዲ ዓረቢያ የቋሚ መኖሪያ ፈቃድ ሕግ ከኾነ፦ የውጭ ሃገራት ሕጋዊ ነዋሪዎች ከዚህ ሕግ ተጠቃሚ ለመኾን የትምህርት፤ የሥልጠና እንዲሁም የገቢያቸው መጠን ትኩረት ውስጥ እንደሚገባ «አራብ ኒውስ» ዘግቧል። አዲሱ የመኖሪያ ፈቃድ ሕግ የውጭ ሃገራት ነዋሪዎች በሣዑዲ ዓረቢያ ባሕል ተሳትፎ እንዲኖራቸው ማበረታታት ዓላማው ነው ተብሏል። የሌሎች ሃገራት ባሕልም ሣዑዲ ዓረቢያ ውስጥ ተቀባይነት እንዲኖረው እገዛ እንደሚያደርግ ተገልጧል።
ነቢዩ ሲራክ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ