1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጎጃም ዞኖች የመጓጓዣ አገልግሎት ዛሬ መጀመሩን

ሐሙስ፣ ግንቦት 22 2016

በምዕራብ ጎጃም ዞን የደንበጫ ከተማ ነዋሪን ስለመንገዶች መከፈት አስተያየታቸውን ጠይቀናቸው መንገዶች በሁሉም አቅጣጫ ተከፍተው ተሸከርካሪዎች እየተመላለሱ ነው፣ ሆኖም የባለሶስት እግር ተሸከርካሪዎች በከተማው ውስጥ እንዳይንቀሳቀሱ መከልከላቸውን ገልፀዋል፡፡

https://p.dw.com/p/4gSIZ
በባህር ዳር አዲስ የተገነባው ድልድይ
በባህር ዳር አዲስ የተገነባው ድልድይምስል Alemnnew Mekonnen/DW

ላለፉት 7 ቀናት ተዘግቶ የነበረው የጎጃም ዞኖች የትራንስፖረት አገልግሎት ዛሬ መጀመሩን

ላለፉት 7 ቀናት ተዘግቶ የነበረው የጎጃም ዞኖች የትራንስፖረት አገልግሎት ዛሬ መጀመሩን ተሳፋሪዎችና ነዋሪዎች ተናገሩ፤ ባለፈት ቀናት በተፈጠረው የመንገዶ መዘጋጋት ብዙዎቹ ለእንግልት ተዳርገው ሰንብተዋል፡፡

ሰሞኑን በተለይ በጎጃም ዞኖች ካለፈው ሳምንት ጀምሮ መንገዶች ተዘግተው ሰንብተዋል፣ በአጋጣሚ ከቤታቸው የወጡ ሰዎች ወደ ቤታቸው ለመመለስ ተቸግረውም ነበር በአትክልትና ፍራፍሬ የተሰማሩ ነጋዴዎችም ምርቶቻቸው በመንገድ ተበላሽተው እንደነበር ገልፀውልናል፡፡ መንገዶቹ ከቀናት መዘጋት በኋላ ዛሬ ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸውን አስተያየት ሰጪዎች አመልክተዋል፡፡
አንድ የደብረማርቆስ ነዋሪ ዛሬ ወደ ሌላ ወረዳ ለመሄድ መናኸሪያ ውስጥ መሆናቸውን ነግረውናል፡፡ በምስራቅ ጎጃም ዞን የቢቸና ከተማ ነዋሪም በተመሳሳይ መንገዶች ተከፍተው ወደ ሁሉም አቅጣጫዎች ተሸከርካሪዎች ወደ ደጀን፣ ቁይ ደብረማርቆስና ሞጣ እየተጓዙ ነው ብለዋል፡፡ የባህር ዳር፣ የአዴትና የቡሬ ከተማ ነዋሪዎችም መንገድ በመከፈቱ ወደየቤተሰቦቻቸው እየተመለሱ እንደሆነ ተመሳሳይ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
በምዕራብ ጎጃም ዞን የደንበጫ ከተማ ነዋሪን ስለመንገዶች መከፈት አስተያየታቸውን ጠይቀናቸው መንገዶች በሁሉም አቅታጫ ተከፍተው ተሸከርካሪዎች እየተመላለሱ ነው፣ ሆኖም የባለሶስት እግር ተሸከርካሪዎች በከተማው ውስጥ እንዳይንቀሳቀሱ መከልከላቸውን ገልፀዋል፡፡ባለፉት ጥቂት ዓመታት በአማራ ክልል በተፈጠረው የሰላም መደፍረስ ምክንት መንገዶች በፀጥታ መታጣት ምክንያት እየተዘጉ ህብረተሰቡ በቀላሉ ከቦታ ወደ ቦታ ለመንቀሳቀስ ተቸግሮ እንደነበር ይታወቃል፡፡ አንድ ዓመት ሊሞላው ጥቂት ወራት የቀረው በአማራ ክልል ያለው ግጭት በርካታ ሰብአዊና ቁሳዊ ጉዳት ማድረሱን ሪፖርቶች ያመላክታሉ፡፡
ዓለምነው መኮንን
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር
እሸቴ በቀለ