1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ባገረሸው ግጭት የተሰደዱ የአማራ ተወላጆች በጫካ ውስጥ ለችግር ተጋልጠዋል

ሐሙስ፣ ጥቅምት 1 2016

በኦሮሚያ ክልል ሁሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን አቢ ደንጎሮ ቱሉ ዋዩ በተባለ ቀበሌ በታጣቂዎች መካከል በተፈጠረ ውጊያ የአማራ ተወላጅ የሆኑ እንደሆኑ የሚናገሩ ነዋሪዎች ተፈናቅለው ጫካ ውስት ከገቡ ሳምንት እንደሆናቸው ተናገሩ፣ መንግስት ወደ አካባቢያቸው እንዲመልሳቸውም ጠይቀዋል፣

https://p.dw.com/p/4XSiV
Äthiopien | Wahlen | Oromia

ከሆሮ ጉዱሩ ወላጋ ዞን የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች ለመንግስት የድረስልን ጥሪ

በኦሮሚያ ክልል ሁሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን አቢ ደንጎሮ ቱሉ ዋዩ በተባለ ቀበሌ በታጣቂዎች መካከል በተፈጠረ ውጊያ የአማራ ተወላጅ  እንደሆኑ የሚናገሩ ነዋሪዎች ተፈናቅለው ጫካ ከገቡ ሳምንት እንደሆናቸው ተናገሩ።  መንግስት ወደ አካባቢያቸው እንዲመልሳቸውም ጠይቀዋል፣ ባለፈው ሐሙስ በነበረው ግጭት በሺዎች የሚቆጠሩት እንደተፈናቀሉና በመቶዎች የሚሆኑ ቤቶች እንደተቃጠሉ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፣ በጉዳዩ ዙሪያ ከዞኑና ከከልሉ ባለስልጣናት አስተያየት ለማካተት ደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

ባለፈው ሳምንት ሐሙስ በኦሮሚያ ክልል ሁሮ ጉድሩ ወለጋ አቢ ደንጎሮ ወረዳ ቱሉ ዋዩ በተቀሰቀሰ ግጭት በርካታ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን ጥቃቱን ሸሽተው በአካባቢው ጫካ እንደሰፈሩ የሚናገሩ ተፈናቃዮች ለዶይቼ ቬሌ አመልክተዋል፡፡የምዕራብ ኦሮሚያ ተፈናቃዮች የርዳታ ጥሪ

ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት እንደደረሰ የሚገልፁት እኝሁ ተፈናቃዮች በሺዎች የየሚቆተሩ ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤቶች ደግሞ ተቃጥለዋል ብለዋል፣ በአካባቢው የስልክ አገልግሎት እንደሌለ የሚናገሩት አስተያየት ሰጪዎች ይህን መረጃ የሚሰጡትም ተራራ ላይ ወጥተው እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

ውሀና ምግብ በሌለበት ሁኔታ በከፋ ሁኔታ ላይ እንደሆኑ የሚናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች መንግስት በአስቸኳ ይድረስልን እያሉ ነው፡፡

እርዳታ በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ የአማራ ብሄር ተፈናቃዮች
በኦሮሚያ ክልል ሁሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን አቢ ደንጎሮ ቱሉ ዋዩ በተባለ ቀበሌ በታጣቂዎች መካከል በተፈጠረ ውጊያ የአማራ ተወላጅ የሆኑ እንደሆኑ የሚናገሩ ነዋሪዎች ተፈናቅለው ጫካ ውስት ከገቡ ሳምንት እንደሆናቸው ተናገሩ፣ መንግስት ወደ አካባቢያቸው እንዲመልሳቸውም ጠይቀዋል፣ ባለፈው ሐሙስ በነበረው ግጭት በሺዎች የሚቆጠሩት እንደተፈናቀሉና በመቶዎች የሚሆኑ ቤቶች እንደተቃጠሉ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፣ምስል Alemnew Mekonnen/DW

ከዚህ በፈት እንደዘገብነው በየጊዜው ለሚነሱ ግጭቶች በአካባቢው የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች መንግስትንና “ኦነግ ሸኔ” የተባለውን ታጣቂ ቡድን ተጠያቂ ሲያደርጉ መንግስትና የአካባቢው የኦሮሞ ተወላጆች ደግሞ ፋኖንና የአማራ ሚሊሺያ የሚሏቸውን አካላት ተጠያቂ ያደርጋሉ፡፡ተፈናቃዮች በርዳታ እጦት እየተሰቃዩ ነዉ

በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ አስተያየት ለማካተት ለሆሩ ጉድሩ ወለጋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ለአቶ ምሬሳ ፊጤና ለኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ያደረግኋቸው የስልክ ትሪዎች አልተሳኩም፡፡የምዕራብ ወለጋ ተፈናቃዮች ተማጽኖ

ባለፉት 4 ዓመታት በኦሮሚያ የተለያዩ ዞኖች በተከሰቱ ግጭቶች አንድ ሚሊዮን የሚሆኑ የአማራ ተወላጆች ተፈናቅለው ወደ አማራ ክልል መግባታቸውን የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ኮሚሽን መግለጡ ይታወሳል፡፡

ዓለምነው መኮንን

ታምራት ዲንሳ

እሸቴ በቀለ