ሳይንስ
ቃለ-ምልልስ ከቤተልሔም ደሴ ጋር
ረቡዕ፣ ግንቦት 21 2011ማስታወቂያ
የሐረር ልጅ ናት። የ20 ዓመት ወጣት። የኮምፒዩተር ፕሮግራም መጻፍ (ኮዲንግን) ተክናበታለች። ከኮምፒውተር ጋር የተያያዙ ነገሮች መሥራት የጀመረችው ገና የ10 ዓመት አዳጊ እያለች ነው። እስካሁን አራት መተግበሪያዎችን (አፕልኬሽኖችን) ሠርታለች። ወጣቶች የቴክኖሎጂ እና የፈጠራ ሥራዎችን እንዲሠሩ የሚያበረታታ «ሶልቭ ኢት» የተሰኘ ሀገር አቀፍ ውድድር ታስተባብራለች። ለተወዳዳሪዎቹ እና ለሌሎች ወጣቶችም የኮምፕውተር ፕሮግራም መጻፍ (ኮዲንግ) ስልጠና ትሰጣለች። ቤተልሔም ደሴ ትባላለች።
ገና በለጋ ዕድሜዋ ዕውቅና እና ዝና ያተረፈችው ቤተልሔም ከተለያዩ አጋሮች ጋር በመተባበር ወጣቶች የኮምፒውተር ፕሮግራም እና የቴክኖሎጂ ዕውቀት እንዲገበዩ እያደረገች ትገኛለች። ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የፈጠራ ክህሎታቸው እንዲዳብር እንደምትሻ የምትናገረው ቤተልሔም እያከናወነቻቸው ስላለቻቸው ጉዳዮች ከዶይቼ ቬለ ለቀረቡላት ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥታለች። ቤተልሔም ከዓመታት በፊት ስለሰራቸው መተግበሪያ፣ በአስተባባሪነት ስለምትመራው የኮምፒውተር ቴክኖሎጂ እና የፈጠራ ውድድር እንደዚሁም ለወጣቶች ስለምትሰጣቸው ስልጠናዎች አብራርታለች።
ሙሉ ቃለ ምልልስ ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።
ተስፋለም ወልደየስ
ሸዋዬ ለገሠ