ስደተኞችን ለመግታት የአዉሮጳ ዕቅድ2 ሰኔ 2008ሐሙስ፣ ሰኔ 2 2008ለስደት ምክንያት የሆኑትን ነገሮች አብረን እናስወግድ በሚል መርህ ስር የአዉሮጳ ማኅበረሰብ አንድ ሃሳብ አጠናቅሮ ለአፍሪቃ መንግሥታት ለማቅረብ ወስኗል። ሃሳቡ ቀደም ሲል ከቱርክ ጋር በዚሁ መስመር የገቡትን ዉል ያስታዉሳል የሚሉ ቢኖሩም ብዙዎች በተቃራኒዉ ከዚያ ይለያል በሚል ተችተዋል።https://p.dw.com/p/1J3tJምስል Getty Images/AFP/O. Koseማስታወቂያ[No title]To play this audio please enable JavaScript, and consider upgrading to a web browser that supports HTML5 audio ትናንት በርሊን ላይ በዚህ ላይ ለመወያየት በርሊን ላይ የተሰባሰቡት አንዳንድ የጀርመን ምክር ቤት አባላት እና የአፍሪቃ ጉዳይ ጠበብት ይህ አዉሮጳ ከእንግዲህ ስደተኞች እንዳይመጡባት ለማድረግ ያቀደችዉ ስልት ነዉ በማለት ሃሳቡን ተቃዉመዋል። ጉዳዩን የተከታተለዉ የበርሊኑ ዘጋቢያችን ይልማ ኃይለሚካኤል ዝርዝሩን ልኮልናል። ይልማ ኃይለሚካኤል ሸዋዬ ለገሠ ኂሩት መለሰ