ስደተኞችን ማገድ ያለዉሙት ትራምፕ
ሐሙስ፣ ጥር 18 2009ማስታወቂያ
በትናንታናዉ ዕለት ታዲያ ሕገወጥ ተሰዳጆች ይገቡበታል ያሉትን ከሜክሲኮ ጋር ሀገራቸዉን የሚያዋስነዉን የድንበር አካባቢ በግንብ ለማጠር ትዕዛዝ አስተላልፈዋል። ዉሳኔያቸዉ ያስቆጣት ጎረቤት ሜክሲኮም እንደሚሉት የግንቡን ወጪ አልከፍልም ብላለች። ትራምፕ በዚህ አላበቁም ለሽብር ስጋት ካሏቸዉ ኢራቅ፣ ሶርያ፣ ኢራን፣ ሱዳን፣ ሊቢያ፣ ሶማሊያ እና የመን ለ30 ቀናት የይለፍ ወይም ቪዛ ፈቃድ ጥያቄ እንዲያዝ የሚያደርግ መመሪያም እያወጡ ነዉ። አዲሱ የአሜሪካን ፕሬዝደንት የፎከሩትን ተግባራዊ ከማድረጋቸዉ አስቀድሞ ለጥቂት ወደ አሜሪካ የገቡ ተሰዳጆች መኖራቸዉን የዋሽንግተኑ ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋ በላከዉ ዘገባ ጠቅሷል።
መክብብ ሸዋ
ሸዋዬ ለገሠ
አዜብ ታደሰ