ስኬታማ ኤርትራውያን በጀርመን
ማክሰኞ፣ ሰኔ 30 2007ማስታወቂያ
ከቅርብ ዓመታት ወዲሕ ሥለ ኤርትራና ኤርትራዉያን ተደጋግሞና ደምቆ የሚሰማዉ የአፍሪቃ ቀንዲቱ ሀገር የአምባገነኖች ጭቆና እና ግፍ ያየለባት ሥለ መሆኗ ነዉ። ስለሆነም በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ የሐገሪቱ ዜጎች ግፉን ሽሽት ወደ ተለያዩ የዓለም ክፍሎች በተለይም ወደ አዉሮጳ ይሰደዳሉ ወይም ለመሰደድ ሲሞክሩ በየበረሐና ባሕሩ ያልቃሉ።የፍራንክፈርቱ ወኪላችን ጎይቶም ቢሆን ፤ እንደሚለዉ ግን በስደት ለሥቃይ እና እንግልት ከተጋለጡት መካከል የተሳካላቸዉ ኤርትራዉያንም አሉ።የዛሬ አዉሮጳና ጀርመን ርዕስ ነዉ።
ጎይቶም ቢሆን
ልደት አበበ
ነጋሽ መሐመድ