ስለ ሕዝበ ውሳኔው የቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች ምን ይላሉ ?
ረቡዕ፣ መስከረም 19 2014ማስታወቂያ
በደቡብ ክልል ውስጥ የሚገኙ አምስት ዞኖችን እና አንድ ልዩ ወረዳን የደቡብ ምዕራብ ሕዝቦች ክልል በተባለ አዲስ ክልል የሚያዋቅር አልያም በነባሩ ክልል እንዲቀጥሉ የሚያደርግ የህዝበ ውሳኔ ነገ ሀሙስ ይከናወናል። የድምጽ መስጫ ቀኑ ለወራት ከተራዘመ በኋላ ነገ እንደሚከናወን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ አድርጓል። በነገው ዕለት ድምፅ ለሚሰጥበት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ህዝበ ውሳኔ መራጮች ምን ይላሉ ለሚለው በከፋ ዞን ቦንጋ ከተማ የሚገኘው የዶቼ ቬለ (DW) ዘጋቢ ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ የነዋሪዎቹን አስተያየት ያሰባሰበበትን ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ታምራት ዲንሳ
አዜብ ታደሰ