ሴራሊዮን በኢቦላ ተሐዋሲ ፍራቻ መዲናዋን በከፊል ዘጋች
ቅዳሜ፣ የካቲት 7 2007ማስታወቂያ
ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢቦላ ተሐዋሲን በተመለከተ በሀገሪቱ የተመደበ አንድ የሒሳብ አጣሪ ወይም ኦዲተር የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ለኢቦላ ድንገተኛ አደጋ በሚል ከተሰበሰበው 17 ሚሊዮን ዩሮ ውስጥ አንድ ሦስተኛውን ያህል ያለምንም ተጠያቂነት አባክነዋል ሲል አጋልጧል። ባከነ የተባለው ገንዘብ በአብዛኛው ከግብር እና በርዳታ ከተገኙ ድጋፎች ጋር ተያያዥነት ያለው መሆኑም ተጠቅሷል። ይህ የባከነ ገንዘብ ግን ኢቦላን ለመከላከል በሚል ለሴራሊዮን በተመድ ከተመደበው አለያም ከዓለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የተሰበሰበውን ገንዘብ የሚመለከት አለመሆኑም ተነግሯል። ለኢቦላ መከላከል ተሰብስቦ እንደባከነ የተጠቀሰው በሚሊዮን የሚቆጠር ዩሮ በመንግሥት በኩል ለጤና ባለሙያዎች የአገልግሎት ክፍያ፣ የመድሐኒት እና የህክምና ቁሳቁስ መግዢያ ውሏል መባሉም ተገልጧል።
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ልደት አበበ