ሳይንስ፤ ሥ/ቴክኒክና ፈጠራ
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 10 2004ማስታወቂያ
የፈጠራ ውጤት መሆኑን ከተገነዘበ ውሎ አድሯል። በመሆኑም፤ የተፈጥሮ ሳይንስና ሂሳብ ፣ በከፍተኛ ደረጃ የሚቀሰምባቸው ተቋማትን ለማስፋፋት ካለ እቅድና ጥረት ባሻገር፤ ዕድገትን ማፋጠን ስለሚቻልበት ሁኔታ መመከሩ አልቀረም። ይሁንና በሳይንስና ሥነ ቴክኒክ እንዲሁም የፈጠራ ወጤት ላይ አፍሪቃውያን አንድ መድረክ ፈጥረው ሲመክሩ ፤ በቅርቡ በናይሮቢ ፤ ኬንያ ፣ የተካሄደው በዓይነቱ የመጀመሪያው መሆኑ ነው የተነገረው።
ከክፍለ ዓለሙ 4 ማዕዘናት የተሰባሰቡ፣ የሳይንስና ሥነ ቴክኒክ ጠበብት እንዲሁም የየሀገራቱ የሳይንስና ሥነ ቴክኒክ ሚንስትሮች፤ ናይሮቢ ውስጥ ከመጋቢት 21 እስከ 23,2004 ፣ የ 3 ቀናት ጉባዔ ማካሄዳቸው ታውቋል። ኢትዮጵያን በመወከል በጉባዔው ተገኝተው ከነበሩት መካከል፣ የኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር ፣ ሚንስትር ደኤታ፣ አቶ መሐሙዳ ጋዝ ይገኙበታል። ከእንዲያ ዓይነቱ፣ የሳይንስና ሥነ ቴክኒክ ጉባዔ፣ በአጠቃላይ ለአፍሪቃው ክፍለ ዓለም፣ በተናጠልም ኢትዮጵያን ለመሳሰሉ ሀገራት የሚቀሰመው ጠቃሚ ጉዳይ ምን ይሆን? ክቡር ሚንስትሩን ጠይቄአቸው ነበር---
ተክሌ የኋላ
ነጋሽ መሐመድ