ሳዑዲ ድንበር የሚገኙ ከ 500 በላይ እስረኞች ድረሱልን እያሉ ነዉ
ሐሙስ፣ ሐምሌ 4 2011ማስታወቂያ
ከ 500 በላይ የሚሆኑና በየመን እና በሳዉዲአረብያ ድንበር ላይ በሚገኝ እስርቤት የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን አቤቱታችን ለመንግሥት ንገሩልን ሲሉ ገለፁ። በእስር ቤት የሚገኙት የእፅ አዛዋዋሬ ኢትዮጵያዉያን እስረኞች በጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ጥያቄ የተቀነሰልን የእስር ጊዜ ተግባራዊ አልሆነም፤ ታማሚ የሆነዉም የሕክምና ክትትል ተነፍገናል ሲሉ ገለፁ። ሳዉዲ አረብያ የሚገኘዉም የኢትዮጵያ ኤንባሲም ለዚህ ችግር መፍትሄ ሊያሰጠን ይችል ነበር ሲሉም ነዉ የተናገሩት። በሌላ በኩል ሳዉዲ አረብያ ዉስጥ በአደንዛዥ እፅ ዝዉዉር የሚከሰሱ ሰዎች ከአንድ አካባቢ የመጡ ሰዎች ናቸዉ፤ የተከበረዉን ኢትዮጵያዊ ስማችንንም አጎደፉብን ሲሉ በበኩላቸዉ ቅሬታቸዉን አሰምተዋል። በጉዳዩ የኢትዮጵያ ኤንባሲን ለማነጋገር ያደረግነዉ ጥረት አልተሳካም።(ፎቶ ከክምችት)
ነብዩ ሲራክ
አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሰ