ሲና በረሀ የታገቱት የኤርትራ ስደተኞች እና የአውሮፓ ፓርላማ
ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 13 2003ማስታወቂያ
በሌላም በኩል የግብፅ መንግስት ታጋቾቹን ለማስለቀቅ የተቻለውን ሁሉ እንዲያደርግ የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ጠይቋል ። ፓርላማው በቅርቡ ባካሄደው ስብሰባ በአካባቢው የሚካሄደው ሀገ ወጥ የሰዎች ዝውውርና በድንበር ላይ የሚገደሉት ስደተኞች ጉዳይ እንደሚያሳስበው አስታውቆ ግብፅ ሲና በረሃ የታገቱትን የኤርትራ ስደተኞችን ለማስለቀቅ መንግስት ጥረት እንዲያደርግ የሚያሳስብ ውሳኔ አሳልፏል ። በመንግስታቱ ድርጅት የስደተኛ ቻርተር መሰረት ፣ መንግስት ለስደተኛ ጥበቃ ሊያደርግ እና ተገንም ሊሰጥ እንደሚገባም ፓርላማው በውሳኔው አስታውቋል ። ውሳኔውን መነሻ በማድረግ የብራሰልሱ ዘጋቢያችን የፓርላማውን የልማት ኮሚሽነር እንዲሁም የስደተኞች ካውንስል ቃል አቀባዮችን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል ።
ገበያው ንጉሴ
ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሰ