ሱ ጉትንበርግ ተሰናበቱ
ረቡዕ፣ የካቲት 23 2003ማስታወቂያ
በጀርመን ህዝብ ዘንዳ ከፍተኛ ተወዳጅነት ያላቸው ሱ ጉትንበርግ ስልጣናቸውን የለቀቁት በደቡብ ጀርመን የሚገኘው የ ባይሮይት ዩኒቨርስቲ ባለፈው ሳምንት የዶክተርነት ማዕረጋቸውን ከሻረ ወዲህ ከፖለቲካውና ከአካዳሚው ዘርፍ በገጠማቸው ብርቱ ግፊት የተነሳ ነው። « ከመራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ጋ በወዳጅነት መንፈስ ባደረጉት ውይይት ላይ የፖለቲካ ስልጣኔን በጠቅላላ እንደምለቅ በመግለጽ እንዲያሰናብቱኝ ጠይቄአለሁ። »
ሱ ጉትንበርግ ለመመረቂያ ባቀረቡት ጥናት ላይ የተጠቀሙባቸውን የሌሎች ሰዎች ሀሳቦችን፡ ግልጽ በሆነ ሳይንሳዊ መንገድ በማመላከት ፈንታ፡ እንደራሳቸው አድርገው ማቅረባቸው ነው የዶክተርነት ማዕረጋቸው እንዲገፈፍ ምክንያት የሆነው። ሱ ጉትንበርግ በስልጣናቸው እንዲቆዩ በይፋ የደገፉዋቸውን መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክልን ለዚሁ ድጋፋቸው ከልብ አመስግነዋል።