ሰማያዊ ፓርቲና ሰላማዊ ሰልፎቹ21 መጋቢት 2007ሰኞ፣ መጋቢት 21 2007ሰማያዊ ፓርቲ፣ ትናንት በ 15 የተለያዩ ከተሞች ሊያካሂድ ያሰበውን ሰላማዊ ሰልፍ ከ 4 ከተሞች በስተቀር በፖሊስ መደናቀፉን የፓርቲው ሊቀመንበር ገለጡ። አዲስ አበባ የተጠራዉ ሰልፍ በታቀደዉ መንገድ መሄድ ባለ መቻሉ ተቃዉሞ ሰልፉ ከጽ/ቤቱ ብዙም ሳይርቅ መደረጉ ተመልክቶአልhttps://p.dw.com/p/1Ezgqምስል DW/Y. G/Egziabherማስታወቂያ በአዲስ አበባ ሊካሄድ የታቀደውም፤ ሰልፈኞቹ፤ ከካዛንቺስ ከሚገኘው ጽ/ቤታቸው ተነሥተው በአራት ኪሎ በኩል «ወደ ቤል ኤር» ሜዳ ለማምራት ሲንቀሳቀሱ፣ፖሊስ፣ «ባልተፈቀደላችሁ የጉዞ መሥመር መጓዝ አትችሉም በማለቱ ፤ እዚያው ፓርቲው ጽ/ቤት አጠገብ ሰልፉ ተጠናቅቋል። ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ተክሌ የኋላ ሂሩት መለሰ