ሰላማዊ ሰልፍ በድሬዳዋ
ማክሰኞ፣ መስከረም 27 2012ማስታወቂያ
በድሬደዋ ደቻቱ፣ አምስተኛ እና ገንደ ጋራ በተባሉ አካባቢዎች ለተከሰተው ግጭት መንግስት መፍትሄ ይስጠን ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ትናንት እና ዛሬ ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ ጠየቁ። በትናንትናው ዕለት በደቻቱ አከባቢ የሚኖሩ ሴቶች ያካሄዱት ዓይነት ሰላማዊ ሰልፍ በዛሬው ዕለት ወንዶችም ሴቶችም በተገኙበት በአምስተኛ እና ገንደ ጋራ ተካሂዷል። በዛሬው ዕለት በአስተዳደሩ ህንፃ ፊት ለፊት ተገኝተው ተቃውሞ እና ጥያቄ ያቀረቡት የኅብረተሰቡ አካላት «ችግር ፈጣሪዎች ተጠያቂ ይሁኑ፣ አስተዳደሩ በየጊዜው ለሚፈጠረው ግጭት ዘላቂ መፍትሄ ይስጥ» የሚሉ እና ሌሎች ጥያቄዎችም አቅርበዋል።
መሳይ ተክሉ
ኂሩት መለሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ