1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሞስኮን ከምዕራባውያን ያፋጠጠው የሩሲያ አራት ግዛቶች ግንጠላ

ሰኞ፣ መስከረም 23 2015

ሩሲያ አራት የዩክሬን ግዛቶች ገንጥላ ባለፈው ሳምንት ጠቅልላች። ዶኔትስክ፣ ሉሐንስክ፣ ኼርሶን እና ዛፖሬዥያ በተባሉት ግዛቶች የተካሔደውን ሕዝበ ውሳኔ ግን ዩክሬን እና አጋሮቿ ሕገ ወጥ እና የይስሙላ ብለውታል። የሩሲያ እርምጃ፤ ሰባት ወር ለዘለቀው ጦርነት ማብቂያ ወይስ የበለጠ ውድመትና ጥፋት ሊያከትል ለሚችል ትልቅ ጦርነት መቃረቢያ?

https://p.dw.com/p/4Hh9Y
Ukraine | Krieg | Ukrainische Flagge im Dorf Dolyna
ምስል Metin Aktas/AA/picture alliance

ማሕደረ ዜና፦ ሞስኮን ከምዕራባውያን ያፋጠጠው የሩሲያ አራት ግዛቶች ግንጠላ

ዩክሬንን ከማውደም ሩሲያን ከማዳከም አልፎ አውርፓንም ለከፍተኛ የደህንነት ስጋት፤ ለሀይል አቅርቦት ዕጥረትና የኑሮ ውድነት ያጋለጠው የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት; ከመብረድ መቀነስ ይልቅ ግሎና ተስፋፍቶ የአለምን ሰላም ጭምር እንዳያውክ አስጋቷል፡፤ ስጋቱ የመጣውና ውጥረቱ የነገሰው ባለፈው ዓርብ ሩሲያ; በእስካሁኑ ጦርነት ያየዘቻቸውን አራት የዩክሬን ግዛቶች እስክወዲያኛው ድረስ የሩሲያ አካል አድርጋ የጠቀለለቻቸው መሆኑን በይፋ በማሳወቋ ነው። ሩሲያ ከእንግዲህ ከእነዚህ ግዛቶች ውጭ በሌሎች ጉዳዮች ከዩክሬን ጋር በመደራደር ሰላም ለመፈጠር ዝግጁነቷን ስትገልጽ፤ ዩክሬን ግን ዋናው ጦርነት የተጀመረው አሁን ነው በማለት ለረጅሙ ጦርነት ዝግጁ መሆኗን አስታውቃለች። አሜሪካና አውሮፓ የሩሲያን እርምጃ በማውገዝ ቁጣ ፉከራቸውን ሲገልጹ፤ የተቀረው ዓለም ደግሞ ሁኔታውን በአርምሞ እየተከታተለው ነው።  

ከቀዝቃዛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ በኋላ፤ ትልቋ የሶቭየት ህብረት ስትፈረካከስ ከተፈጠሩት ነጻ አገሮች ውስጥ፤ ይበልጥ የምዕራባውያንና ሩሲያ መቆራቆሻ ሜዳ ሆና እስካሁን የዘለቀችው አገር ዩክሬን ናት።  በዩክሬን በተከታታይ ወደ ስልጣን የሚመጡት መንግስታት በስልጣን ለመቆየት ከህዝባቸው ይልቅ የምእራባውያንን ወይም የሩሲያኖችን ድጋፍ የሚያማትሩ መሆናቸው፤ ለነዚህ አሁን በመካሄድ ላይ ባለው ጦርነት በቀጥታም ይሁን በተዘውዋሪ ለገቡ ሀይሎች  በር የከፈተ መሆኑ ተደጋግሞ ይጠቀሳል።  

አውሮፓና ምዕራባውያን ባጠቃላይ የበርሊንን ግንብ መፍረስ ተከትሎ፤ ከሶቭየት ህብረት የወጡትን የምስራቅ አውርፓና ቦልቲክ አገሮች ወደ ህብረቱና ኔቶ በማስገባት በነሱ ተጽኖ ስር ማስገባታቸው የሚታወቅ ሲሆን፤ ባንጻሩ ሩሲያ በዚያን ወቅት እራሷንም እንደአገር ለማስቀጠል በብዙ ውጣውረድ ማለፍ ነበረባት።

Russland | Zeremonie zur Annexion ukrainischer Gebiete | Rede Putin
የዶንቴስክ፣ ሉሃንስክ፣ ዣፖሪዚያ እና ኬሄርሶን ግዛቶች በሙሉና ባብዛኛው በሩሲያ ቁጥጥር ሆነው የቆዩ ሲሆን፤ ቀደም ብሎ በተካሂደ የህዝበ ውስኔ መሰረትም ባለፈው ዓርብ ግዛቶቹ ወደ ሩሲያ የተጠቃለሉ መሆኑን ፕሬዝዳንት ፑቲንና የግዛቶቹ ተወካዮች ባካሄዱት ደማቅና በአገሪቱ ቴሌቪዥን በቀጥታ በተላለፈ ስነ ስርዓት ይፋ ሁኗል። ምስል AP Photo/picture alliance

የሶቭየቱ ጎራ ወታደራዊ ተቁም የነበረው ዋርሶ ፓክት ሲፈርስ፤ ተፎካካሪ የነበረው የምእራባውያኑ ወታደራዊ ተቋም፤ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ኔቶም መስፋፋቱን እንዲያቆም መግባባት ነበር ቢባልም፤ እሱ ግን ብዙዎቹን የምስራቅ አውሮፓና ቦልቲክ የቀድሞ የሶቭየት ግዛቶችን አባሎቹ ማድረግ ነበር የቀጠለው ። ሩሲያ በበኩሏ፤ በተለይ ፕሬዝዳንት ፑቲን ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ተጠናክራ እራሷን የቀድሞው የሶቭየት ህብረት ወራሽ አድርጋ ሲትወጣ፤ የምራባውያንን በተለይም የኔቶን ከሩሲያ ጫፍ ድረስ መስፋፋት መጠየቅ ጀመረች። ምራባውያን ስጋት ነው የሚሉት የምስራቁ ጎራ የጦር ቡድን የነበረው ዋርሶ ፓክት ከፈረሰ በኋላ፤ ኔቶ በዚህ መጠን መስፋፋቱ በአካባቢውና በዓለም ላይ አዣዥ ናዛዥ ለመሆን ነው በሚል፤ አጥብቃ ተቃወመችው። በተለይ ዩክሬንን ወደ ኔቶ ለማስገብት የሚደረገውን ጥረት የራሷ የጽጥታ ስጋት አድርጋ በመቁጠር አጥብቃ ነው ስትቃወም የቆየችው። በዩክሬን ምስራቃዊ ግዛቶች የሚኖሩ የሩሲያ ቃንቋ ተናጋሪዎች እምነት ቋንቋና፤ ባህል ከሩሲያ ጋር ተመሣሣይ በመሆኑም፤ በአፍቃሪ ምራባውያን የኬቭ መንግስት ጥቃት ይፈጽምባቸዋል በማለትም ስትከራከር ቆይታለች።   

የምራባውያን ከቻይናና ሩሲያ ጋር ያላቸው ልዩነት እየሰፋና መፈራረጅ ሲመጣ፤ ዩክሬንም ወዳውሮፓ ህብረትና ኔቶ እየቀረበች ስትሄድ፤ ፕሬዝዳንት ፑቲን ዛሬ ሰባት ወር ያለፈውንና ዩክሬንን ከናዚ ቅሬቶች የማጽዳትና በሩሲያ  ቁንቋ ተናጋሪዎች ላይ የተቃጣውን ጥቃት ለመክላከል ያለመ ነው ያሉትን ወታደራዊ ዘመቻ ከፈቱ። በመጀመሪዎቹ  የጦርነት ሳምንታት፤ ጦርነቱ መላ ዩክሬንን አካቶ የነበር ቢሆንም፣ በሁዋላ ግን ሩሲያ  ይዞታዋን የሩሲያ ቋንቁ ተናጋሪ በሆኑ የምስራቅና ደቡብ ምስራቅ ግዛቶች፤ እጠናክራ ቆይታለች። በዚህም መሰረት  የዶንቴስክ፣ ሉሃንስክ፣ ዣፖሪዚያ እና ኬሄርሶን ግዛቶች በሙሉና ባብዛኛው በሩሲያ ቁጥጥር ሆነው የቆዩ ሲሆን፤ ቀደም ብሎ በተካሂደ የህዝበ ውስኔ መሰረትም ባለፈው ዓርብ ግዛቶቹ ወደ ሩሲያ የተጠቃለሉ መሆኑን ፕሬዝዳንት ፑቲንና የግዛቶቹ ተወካዮች ባካሄዱት ደማቅና በአገሪቱ ቴሌቪዥን በቀጥታ በተላለፈ ስነ ስርዓት ይፋ ሁኗል።  

Russland | Zeremonie zur Annexion ukrainischer Gebiete | Putin mit den Besatzungschefs
ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን በንግግራቸው፤ እያካሂዱት ያለው ጦርነት ምዕራባውያን ሩሲያን ለማዳከምና ህዝቧንም አንገቱን ለማስደፋት ያሚያደርጉትን ጥረት ለመቋቋምና የሩሲያን ህልውናና ክብር ለማስቀጠል   የሚደረግ  ትግል መሆኑን ጫና ሰተውታል። ምስል Grigory Sysoyev/AP Photo/picture alliance

በስነ ስርዓቱ ላይ ፕሬዝዳንት ፑቲን ባሰሙት ዘለግ ያለ ንግግርም፤ አራቱ የዶንቴስክ ሉሃንስክ ሻፖሪዚያና  ኬሄረሶን  ግዛቶች የዩክሬን አካል ሆኖ የመቀጠላቸው  ሁኔታ ያበቃ መሆኑንና ሁልግዜም ሩሲያ ሆነው እንደሚቆዩ አስታውቀዋል። 
ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው፤ እያካሂዱት ያለው ጦርነት ምዕራባውያን ሩሲያን ለማዳከምና ህዝቧንም አንገቱን ለማስደፋት ያሚያደርጉትን ጥረት ለመቋቋምና የሩሲያን ህልውናና ክብር ለማስቀጠል   የሚደረግ  ትግል መሆኑን ጫና ሰተውታል። ፕሬዝዳንቱ ከዚህ ቀደም ባልተለመደ  ሁኔታ  ምራባውያን በሩሲያ ብቻ ሳይሆን በሌሎች የዓለም ክፍሎች በሚገኙ አገሮችና አህዝቦች ላይም ከፍተኛ በደል የፈጽሙ መሆኑን የቅኝ ግዛት ታሪክን በመጥቀስ ጭምር ደመኛ ጠላት አድርገው ፈርጀዋቸዋል   
ፑቲን ቀደም ብሎ በሰጡት አስተያየት  ያገራቸው ደህንነት አደጋ ላይ ከወደቀ የኒውክለር መሳሪይ ጭምር እንደሚጠቀሙ ያስታወቁበትን ሁኔታ በማሳትወስም፤ አሜርካ እ እ እ በ1945 ዓም ጦርነት በሌለበት ወይም ባበቃበት ሁኒታ ሁለት የኒውክለር ቦምቦችን በማፈንዳት በሰውና በተፍጥሮ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰች ናት በማለት በዚህ ጉዳይ አስተያየት ወይም ትችት ለመስጠት ትክክለኛዋ አገር አለመሆኗን አመላክተዋል። 
የግዛቶቹን ወደ ሩስያ የመጠቅለሉ ስነስራትና  ፕሬዝዳንት ፑቲን ያሰሙት ንግግር፤ በተለይ ለሶቭየት ዘመን ናፋቂዎች ሩስያውያን ትልቅ ደስታ እንደሚሰጣቸው የታወቀ ነው። በጦርነቱ ጫናና የክተቱ ጥሪ ምክኒያት እየቀነሰ ነው የተባለውን የፕሪዝዳንት ፑቲን ድጋፍ በመጠኑም ቢሆን ሊጭምረው እንደምችልም ይገመታል። 
በዚህ የሩሲያ እርምጃና የፕሬዝዳንት ፑቲን ንግግር በዋናነት የተከፉት ዩክሬኖችና መሪያቸው ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ መሆናቸው ግልጽ ነው።  ዘሌንስኪ እርምጃውን በማውገዝ ዓለም በሙሉ በሩሲያ ላይ እንዲነሳ ለመንግስታቱ ድርጅትና ለመንግስታት ጥሪ አቅርበዋል፤ ጦርነቱንም እስከ ድል ድረስ እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።  

Ukraine Kiew | Wolodymyr Selenskyj, Präsident
ፕሬዝደንት ቮሎዶሚር ዘሌንስኪ እርምጃውን በማውገዝ ዓለም በሙሉ በሩሲያ ላይ እንዲነሳ ለመንግስታቱ ድርጅትና ለመንግስታት ጥሪ አቅርበዋል፤ ጦርነቱንም እስከ ድል ድረስ እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።  ምስል Ukrainian Presidential Press Office/AP Photo/picture alliance

የመንግስታቱ ድርጅት፤ አሜሪካ፤ የአውሮፓ ህብረትና አባል አገገራቱ፤ የፕሬዝዳንት ፑቲንን እርምጃ  በክፍተኛ ደረጃ በማውገዝ፤ ድርጊቱን ህገወጥ፣ የመንግስታቱ ድርጅትን ደንብ፤ የሚጥስና እውቅና ሊሰጠው የማይችል ነው በማለት ኮንነው ዩክሬን፤ በጦርነቱ እንድተገፋና  ከጎኗም እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል።   

የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸህፊ ሚስተር አንቶኒዮ ጉቴሬሽ ባስተላለፉት መልክት፤ ማንኛውም በኃይል የሚደረግ የግዛት ነጠቃ የመንግስታቱ ድርጅትን ቻርተር የሚቃረን በመሆኑ፤ ሉሃንስክን ዶንተስክን ዣፕሮዢንና ኬሄርሶን ግዛቶችን ወደሩሲያ ለመጠቅለል የሚወሰደው እርምጃ ምንም ዓይነት ህጋዊነት የለውም ብለዋል። 
ፕሬዝድንት ባይደን በበኩላቸው፤ “መቼም ቢሆን ሩሲያ ከዩክሬን ሉዑላዊ ግዛት ውስጥ የኔ ነው የምትለውን አሜሪካ አትቀበልም።ተካሄደ የሚባለው ህዝበ ውሳኔና ውጤቱ በሞስኮ የተቀመረ ተራ ጨዋታ ነው” በማለት ለዩክሬን የሚሰጡትንን ድጋፍ አጠንናክረው የሚቀጥሉ ብቻ ሳይሆን ሌሎች አገሮችም ድርጊቱን እንዲያወግዙና ሩሲያን እንዲያገሉ እንደሚጥሩ አስታውቀዋል። 
የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሀላፊ ሚስተር ጆሴፕ ቦርየል በህብረቱ አገሮች ስም ባስተላለፉት መልክትም ሁሉም አባል ገሮች ሩሲያንና ሚስተር ፑቲንንን ማውገዛቸውን አስታውቀዋል። “ይህንን  በህሰት የተቀመረ ውጤት የአውሮፓ ህብረት አባል አገሮች እንደማይቀበሉት በሁሉም 27ቱ አባል ገሮች አገሮች ስም መናገር እችላለሁ” በማለት የህብረቱንና አባል አገሮቹን አቁም ግልጽ አድርገዋል። 
የኔቶ ዋና ጸሀፊ ሚስተር ስቶልቴንበርግ በበኩላቸው ፕሬዝዳንት ፑቲንና መንግስታቸው የፈጸሙት ህገወጥ የመሬት ወረራ ነው ሲሉ ሁሉም አባል አገሮች ድርጊቱን እንዲያውግዙ ጥሪ አርበዋል   
ከዚህ የሞስኮ ዳንኪራና ከኒውዮርክና ያውሮፓ ከተሞች ውግዘት በኋላ የፕሬዝድንት ፑቲን ቀጣይ እርምጃ ምን ይሆናል? በዩክሬን እየነደደ ያለው የጦርነት እሳትስ ይበርድ  ይሆን ወይ?  የምራባውያንና ሩሲያ ግንኑነት ወዴት እይሄደ ነው? የሚሉት እየተነሱ ያሉ ዋና ዋና ዋና ጥያቄዎች ናቸው።    
 ሚስተር ፑቲን  ከነዚህ ከተጠቃለሉት ግዛቶች በመለስ  ከዩክሬን ጋር ለመደራደርና ስላም ለመፍጠር ዝግጁ መሆናቸውን መናገራቸው ተሰምቷል።ዘሌንስኪ ግን ጦርነቱን አጠናክረው እንደሚቀጥሉና ሩሲያን ከሁሉም የየዩክሬን ግዛቶች በሀይል ጠቅልለው ማስወጣታቸው እንደማይቀር ነው የሚናገሩት። የኔቶ አባል ለመሆንም በልዩ ሁኒታ እንዲፈቀድላቸው ጥያቄ ያቀረቡ መሆኑ ተገልጿል። ሆኖም ግን የሁሉንም አባል አገሮችን ስምምነት የሚጠይቀው የአባልነት  ጥያቄ  መሣካቱ ሲበዛ ያጠራጥራል  ። 

Antonio Guterres
የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸህፊ ሚስተር አንቶኒዮ ጉቴሬሽ ባስተላለፉት መልክት፤ ማንኛውም በኃይል የሚደረግ የግዛት ነጠቃ የመንግስታቱ ድርጅትን ቻርተር የሚቃረን በመሆኑ፤ ሉሃንስክን ዶንተስክን ዣፕሮዢንና ኬሄርሶን ግዛቶችን ወደሩሲያ ለመጠቅለል የሚወሰደው እርምጃ ምንም ዓይነት ህጋዊነት የለውም ብለዋል። ምስል Lokman Vural Elibol/AA/picture alliance

በመሆኑም  የፕርሬዝዳንት ፑቲን ውሳኔና እርምጃ እንዲሁም በሩሲያ ላይ ዩክሬንና አጋሮቿ እያዥጎደጎዱት ለው የውግዘት መግለጫና ፉከራ፤ ዩክሬን ላልተወሰነ ግዜ በጦርነት መቀጠሏ የማይቀር መሆኗን ብቻ ሳይሆን ጦርነቱ ሌሎችንም የማስገባትና የመስፋት ዕድል ሊኖረው እንደሚችል ነው የፖለቲክ ተንታኞች የሚናገሩት። እነዚሁ አስተያየት ሰጭዎች ፕሬዝዳንት ፑቲን በዚህ እርምጃቸው የጦርነቱን ሁኔታ ለውጠውታል፤ ህጋዊነትም አላብሰውታል ይላሉ።፡ ጦርነቱ ቀደም ሲል በዩኪሬን ግዛት የነበር ሲሆን፤ ካለፈው ዓርብ ጀምሮ ግን ጦርነቱ በሩሲያ ሉአላዊ  ግዛት ውስጥ  በሆኑት በዶንቴስክ፣ ሉህንስክ፣ ዣፖራዛና ኬሄሮስን ነው የሚካሄደው። ሩስያ የምታደርገው ጦርነት ህጋዊና ሉዑላዊነት የማስከበር ጦርነት ሆኖ፤ ባንጻሩ ዩክሬን በሩሲያ ግዛት ላይ ሺብር ፈጣሪ፤ እሷን የሚደግፉ  ምራባውያን ደግሞ በሉአላዊር አገር ውስጥ ጣልቃ የሚገቡ ያሸባሪ ቡድን ደጋፊዎች ተብለው ሊፈረጁ ነው በሩሲያ በኩል። በእርግጥ ጦርነት እየተካሄደ ባለበት ወቅት የሚካሄድ ህዝበ ውስኔ በጠመንጃ አስገድዶ የሚፈጸም ስለሚሆን ተተቀባይነት የለውም የሚለው ክርክር የሩሲያን ድርጊት በህግ ፊት የሚያቀለው ሊሆን ይችላል። ግን ደግሞ ሩሲያ በመንግስታቱ ድርጅት ቻርተር የህዝቦችን የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት ድንጋጌ በመጥቀስ መከራክሯ እይተሰማ ነው። እነዚህ ሁሉ እርምጃዎች፤ የፕሪዝደንት ፑቲን ጸረ ምራባውያን ዲስኩርና የምራባውያን ፉከራ የአስከፊውን ጦርነት አይቀሬነት የሚጠቁሙ ናቸው በማለት የሚያስጠንቅቅቁ ወገኖች፤ ለሰላም የሚድረገው ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ያቀርባሉ።  

USA | Präsident Joe Biden
ፕሬዝድንት ባይደን በበኩላቸው፤ “መቼም ቢሆን ሩሲያ ከዩክሬን ሉዑላዊ ግዛት ውስጥ የኔ ነው የምትለውን አሜሪካ አትቀበልም።ተካሄደ የሚባለው ህዝበ ውሳኔና ውጤቱ በሞስኮ የተቀመረ ተራ ጨዋታ ነው” በማለት ለዩክሬን የሚሰጡትንን ድጋፍ አጠንናክረው የሚቀጥሉ ብቻ ሳይሆን ሌሎች አገሮችም ድርጊቱን እንዲያወግዙና ሩሲያን እንዲያገሉ እንደሚጥሩ አስታውቀዋል። ምስል Liu Jie/Xinhua/IMAGO

በአንጻሩ ከዩክሬን ውጭ በተለይ አውሮፓ በዚህ ጦርነት መሰላቸት ብቻ ሳይሆን፤ ከፍተኝ ዋጋ እየክፍለም በመሆኑ፤ ለጦርነቱ ገንዘብ ድጋፍ በሚያፈሱትም ሆነ በሩስያ ላይ የማዕቀብ ጋጋታ በሚያስተላለፉ መሪዎች ላይ ተቃውሞ እየተነሳ መሆኑ እየተነገረ ነው።፡ መንግስታትም  ለአገሮቻችው የኢኮኖሚና ማህበራዊ ችግሮች ቅድሚያ በመስጠት የዩክሬንን ጦርነት ችላ እንዲሉ  የሚገደዱበት ግዜ የደረሰ ነው የሚመስለው።፡የምራብውያን በተለይም የአውሮፓ ህብረት በጦርነቱና ተያያዥ እርምጃዎች ላይ የነበራቸውን አንድነት ይዘው መቀጠላቸውን ብዙዎች ይጠይቃሉ። እነዚህን የመሳሰሉት ሁኔታዎች መንግስታት የዩክሬን ጦርነት ሊበርድ፤ የዓለም ስጋትም ሊወገድ የሚችልበትን ሊላ መንገድ ሊመርጡ ይችላላሉ ብሎ ለማሰብ ሊያግዙ ይችላሉ። ግን ጥያቄው እነዚህ ዋናዎቹ በየመድረኩ ሲዘላለፉ የሚውሉት ፖለቲከኞና መሪዎች፤ በጦርነቶች እሳት የሚለበለቡት፤ በኑሮ ውድነት ምክኒያት ለችግር የተጋለጡት ህዝቦች ስቃይ ምን ያህል ይሰማቸዋል? ምን ያህልስ የሚያዝን ልቦና ይኖርቸዋል? የሚለው ነው። የጦርነት ሳይንስ ሊቃውንት፤ ጦርነትን መቼ እንደሚጀመር እንጂ መቼ እንደሚያልቅ ማወቅ ያስቸግራል እንደሚሉት ሁሉ፤ የዩክሬንን ጦርነት ደግሞ አስቸጋሪ ያደረገው  መቼ እንደሚቆም መገመት አለመቻሉ ብቻ ስይሆን ላለመስፋቱና የበለጠ አውዳሚ ላለመህኑ ዋስትና አለመኖሩ ሁኗል።፡  
ገበያው ንጉሤ
እሸቴ በቀለ