ምክር ቤቱ 122 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት አፀደቀ
ዓርብ፣ ጥር 20 2014ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለፌዴራል መንግሥት የ2014 ወጪ 122 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት አፀደቀ።ምክር ቤቱ ዛሬ ካፀደቀዉ ተጨማሪ በጀት 90 ቢሊዮኑ ለጦር ኃይል፣ 8 ቢሊዮኑ ለችግረኞች የምግብ ዕሕል መግዢያ፣ 8 ቢሊዮኑ ለመጠባበቂያ እና 5 ቢሊዮኑ በጦርነት ለወደሙ የመሠረተ ልማት አዉታሮች መጠገኛ ይዉላል ተብሏል።ምክር ቤቱ ከዚሕ ቀደም ለ12014 የ561.7 ቢሊዮን ብር በጀት አፅድቆ ነበር።አሁን ተጨማሪ በጀት ያስፈለገዉ ጦርነት ባሳደረዉ ጫና ምክንያት እንደሆነ የገንዘብ ሚንስቴር ከወራት በፊት አስታዉቆ ነበር።ተጨማሪዉ በጀት ከሐገር ዉስጥ ብድር የሚሸፈን እንደሆነ ተነግሯል።
ሰለሞን ሙጬ
ነጋሽ መሐመድ
እሸቴ በቀለ