ሙስና እና የመንግሥት ፀረ ሙስና ርምጃ
እሑድ፣ ጥር 14 2009ማስታወቂያ
በቀድሞዉ የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዝደንት ታቦ ኢምቤኪ መሪነት የተካሄደ ሌላ ጥናትም በአምስት ዓመታት ዉስጥ ብቻ ከኢትዮጵያ ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ 10 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ወደ ዉጭ ሸሽቷል የሚል ጥናቱን ያፋ አድርጓል። የኢትዮጵያ መንግሥት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ሙስናን ለመዋጋት ቆርጬ ተነስቻለሁ ሲል ይደመጣል። ለርምጃዉ ማሳያም ከሙስና ጋር በተገናኘ መረጃ አግኝቼባቸዋለሁ ያላቸዉን ከአንድ መቶ የሚበልጡ ግለሰቦች ማሰሩን አስታዉቋል። በሀገሪቱ ሙስና መዋቅራዊ ሆኗል የሚሉት ጉዳዩን በቅርበት የሚያስተዉሉ ወገኖች ገዢዉ ፓርቲ ሙስናን ለማጥፋት ተጀምሯል በሚለዉ ዘመቻዉ ቁርጠኝነቱን ገና አላሳየም። የእስሩ ርምጃም ቅርንጫፎች እንጂ ግንድና ሥሩ ላይ አላነጣጠረም ሲሉ ይተቻሉ። ሙሉ ዉይይቱን ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ
ሸዋዬ ለገሠ
ልደት አበበ