ብዙኃን መገናኛዎች ግጭቶችን ከማባባስ እንዲቆጠቡ ተጠየቀ
ሐሙስ፣ ነሐሴ 21 2012ማስታወቂያ
መገናኛ ብዙኃን እና ማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ግጭቶችን ከማባባስ ተቆጠበዉ ለዘላቂ ሰላም ሚናቸዉን መወጣት እንዳለባቸዉ ተነገረ። «Ethiopia, Centre for Advancement of Rights and Democracy» ማለትም የመብቶችና የዴሞክራሲ ማዕከል በኢትዮጵያ የተሰኘዉ ተቋም ኢትዮጵያ ዉስጥ በዩንቨርስቲዎችና በትላልቅ ተቋማት የታዩትን ግጭቶች አስመልክቶ ባወጣዉ ባለ 54 ገጽ መግለጫ እንዳመለከተዉ ፤ ግጭቶችን በተመለከተ የመንግሥት ብዙኃን መገናኛዎች ሳይቀር ለአንድ ወገን ያደላ ዘገባን ያቀርቡ ነበር ብሎአል።
ዮሃንስ ገብረግዚአብሔር
አዜብ ታደሰ
እሸቴ በቀለ