1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መንግስት በአማራ ክልል በቁጥጥር ስር የዋላቸውን ሰዎች እንዲፈታ ተጠየቁ

ሐሙስ፣ ሰኔ 20 2016

ሰሞኑን በባህር ዳር ከተማ በክልሉ ወቅታዊ የሰላም ጉዳይ ላይ ሲመክሩ የቆዩ ተሳታፊዎች የታሰሩ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞችና ምሁራን በይቅርታና በምህረት እንዲፈቱ ጠይቀዋል። ተሳታፊዎቹ በክልሉ መሳሪያ አንስተው የሚዋጉ ታጣቂዎችም ጥያቄያችውን በሰላማዊ መንገድ ለውይይትና ለድርድር እንዲቀርቡ ስብሰባው ሲጠናቀቅ ባወጡት የአቋም መግለጫ ገልፀዋል።

https://p.dw.com/p/4hZxP
በአማራ ክልል ባህርዳር ከተማ ሰሞኑን በተካሄደው የሰላም ኮንፍረንስ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እና ሌሎች ባለስልጣናት ተገኝተዋል።
በአማራ ክልል ባህርዳር ከተማ ሰሞኑን በተካሄደው የሰላም ኮንፍረንስ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እና ሌሎች ባለስልጣናት ተገኝተዋል። ምስል Alemnew Mekonnen/DW

መንግስት በአማራ ክልል በቁጥጥር ስር የዋላቸውን ሰዎች እንዲፈታ ተጠየቁ

 

ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተውጣጥተው ሰሞኑን በባህር ዳር ከተማ በክልሉ ወቅታዊ የሰላም ጉዳይ ላይ ሲመክሩ የቆዩ ተሳታፊዎች የታሰሩ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞችና ምሁራን በይቅርታና በምህረት እንዲፈቱ ጠይቀዋል። ተሳታፊዎቹ በክልሉ መሳሪያ አንስተው የሚዋጉ ታጣቂዎችም ጥያቄያችውን በሰላማዊ መንገድ ለውይይትና ለድርድር እንዲቀርቡ በስብሰባው ሲጠናቀቅ ባወጡት የአቋም መግለጫ ገልፀዋል።ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው አንድ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁር በበኩላቸው፤ የቀረበውን ጥሪ  መንግስትና በክልሉ መሳሪያ አንስተው የሚዋጉ ታጣቂዎች  ቢቀበሉት መልካም መሆኑን ገልፀዋል። 

መንግስትና ታጣቂዎች የህዝብን ጥያቄ እንዲቀበሉ ተጠየቀ

ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተውጣጥተው ሰሞኑን በባህር ዳር ከተማ በክልሉ ወቅታዊ የሰላም ጉዳይ ላይ ሲመክሩ የቆዩ ተሳታፊዎች የታሰሩ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞችና ምሁራን 
በይቅርታና በምህረት እንዲፈቱ ጠየቁ፣ የአማራና የትግራይ ክልሎች የይገባኛል ጥያቄ የሚያቀርቡባቸውን አካባቢዎች የትግራይ ኃይሎች ሰሞኑን በኃይል መቆጣጠራቸውንም የሰላም ጉባኤ ተሳታፊዎች ነቅፈዋል፡፡ አንድ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁር በአማራ ክልል ለው ቀውስ እንዲቆም መንግስትና በአማራ ክልል መሳሪያ አንስተው የሚዋጉ ታጣቂዎች ህዝቡ ያቀረበውን ጥሪ እንዲቀበሉ ጠይቀዋል፡፡አማራ ክልል የውይይትና ድርድር ጥሪ ቀረበ

በባሕር ዳር ከተማ በክልሉ ወቅታዊ የሰላም ጉዳይ ላይ ሲመክር የሰነበተው የሰላም ጉባኤ ሲጠናቀቅ ተወያዮቹ ባለ 10 ነጥብ የአቋም መግለጫ ያወጡ ሲሆን ከነኚህ ውስጥ በአማራ ክልል ያለውን የፀጥታ ሁኔታ ወደ ተሻለ መንገድ ለመመለስ መንግስት  የታሰሩ ሰዎችን እንዲፈታ የሚጠይቅ ነው፡፡

የአቋም መግለጫው፣ “በክልሉ ውስጥ ከተፈጠረው ችግር ጋር ተያይዞ ተጠርጥረው በህግ ቁጥጥር ስር የዋሉ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ ምሁራንና ተፅዕኖ ፈጣሪ ዜጎች በክልሉ ውስጥ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ይቻል ዘንድ መንግስት በይቅርታና በምህረት ነፃ እንዲወጡ እንዲያደርግ” ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
በአማራ ክልል ታጥቀው ለሚታገሉ ወገኖችና የጉባኤው ተሳታፊዎች “ወንድሞችና እህቶች” ብሎ ለጠራቸው አካላት ጉባኤው ባስተላለፈው መልዕክት ደግሞ  “ ጥያቄያችሁን በሰላማዊ መንገድ ለውይይትና ለድርድር በማቅረብ የወገናችሁን ስቃይ ለመቀነስ እንዲቻል መገዳደል ይብቃን ብላችሁ ወደ ወገናችሁ እንድትቀላቀሉ” ብሏል፡፡  የጉባኤው ተሳታፊዎች በተደጋጋሚ “ወንድሞቻችንና እህቶቻችን” ብሎ ለጠራቸው አካላት መንግስትም በመወያየትና በመደራደር በይቅርታና በክብር እንዲቀበላቸው ሲሉ ነው የሰላም ጉባኤው ተሳታፊዎች በመግለጫቸው ያመለከቱት፡፡
እነኚህ አካላት በውይይትና በድርድር ወደ ማህበረሰቡ ከተቀላቀሉ በኋላ በአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በንቃት በመሳተፍ ያላቸውን ጥያቄም በሰላማዊ መንገድ አቅርበው እንዲፈታ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ሁሉም አካላት የድርሻውን እንዲወጣም ጥሪ ቀርቧል፡፡«በአማራ ክልል የፀጥታ ችግር ከ2.5 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ትምሕርት ቤት አይሄዱም»

በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ በተካሄደው የሰላም ኮንፍረንስ ተሳታፊዎች በከፊል
በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ በተካሄደው የሰላም ኮንፍረንስ ተሳታፊዎች በከፊልምስል Alemnew Mekonnen/DW

የትግራይ ኃይሎች በኃል ከያዟቸው የራያ አላማጣ አካባቢዎች እንዲወጡ የሰላም ጉባኤ ተሳታፊዎች ያሳለፉትን የአቋም መግለጫ በተመለከተ የወሎ አማራ ማንነትና የወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ኃይሉ አበራ የሚከተለውን አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
“መውጣት አለባቸው ትክክል ነው፣ ወረራውን እውቅና መስጠታቸው አንድ ነገር ነው፣ ተሸፋፍኖ ነው የነበረው፣ ክህደቶች ነበሩበት፣ ስምምነቱ አጨቃጫቂ በተባሉ ቦታዎች ታጣቂዎች እንዳይገቡ ነው የሚለው፣ ወረራውን ያካሄዱት በጉልበት ነው፣ ትክክል አለመሆኑን ሁሉም አውቆታል፡፡ ጉዳዩ ግን ከመግለጫ ባለፈ ተግባራዊ መደረግ አለበት፡፡”
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፌደራሊዝምና ሰብአዊ መብቶች ተመራማሪና የህግ ምሁር ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴም ተመሳሳይ አስተያት ሰጥተዋል፡፡ “ የአቋም መግለጫው ተግባራዊ የሚሆን ከሆነ መልክም ነገር ነው፡፡
የሰላም ጉባኤ ተሳታፊዎች ለመንግስትና ለታጣቂ ወገኖች ያሰተላለፉት መልዕክት በክልሉ ሰላም ለማስፈን ጉልህ ድርሻ እንዳለው ጠቁመው ሁለቱም አካላት ለተግባራዊነቱ ዝግጁ እንዲሆኑ  ዶ/ር ሲሳይ ጠይቀዋል፡፡
“ የተሸለ ሀሳብ ነው የቀረበው፣ እነኚህ ሰዎች ተከስሰው ነው እስር ቤት ያሉት፣ በይቅርታና በምህረት ሳሆን ክስ በማቋረጥ ሰዎቹን ከእስር በመልቀቅ ለሰላሙ፣ ለንግግርም፣ ለድርድርም፣ የራሱን አስተዋጥኦ ማድረግ እንደሚችል መንግስት ሆደ ሰፊ መሆን አለበት፣ በትንሹም በትልቁም በማሰር መፍትሔ አይመጣም፣ ስለዚህ መፍትሔው መነጋገር፣ መወያየት ነው፣ ለመወያትና ለመደራደር ደግሞ በዚህ ግጭት ምክንት ታሰሩ ሰዎች ከእስር መፈታት አለባቸው፡፡” ብለዋል፡፡በአማራ ክልል የታወጀው የ10 ወራት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቆይታ ተጠናቆ ይሆን?
ዶ/ር ሲሳይ መሳሪያ ይዘው ጫካ ለገቡ አካላትም የቀረበውን የሰላም ጥሪ እንዲቀበሉ ጠይቀዋል፣“... ይህን ጥሪ በአዎንታዊ መልኩ አይተው፣ ለመነጋገርና ለመደራደር ችግሩን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ራሳቸውን ማዘጋጀት አለባቸው፣ እተባለ ያለውን ምክንት ማሳጣት ጥሩ ይመስለኛል፣ አንዳንዴ የተበታተኑ ስለሆኑ፣ ወኪል ስለሌላቸው፣ ማዕከላዊ አመራር ስለሌላቸው ከማን ጋር እንነጋገራለን የሚል ምክንያት መንግስት ያነሳል፣ አንደራደርም ብለዋል የሚልም ምክንት ይነሳል፣ ስለዚህ እነኚህን ምክንቶች በሚያሳጣ መልኩ ለመደራደር ዝግጁ መሆናቸውን ማሳየት አለባቸው፣ ሁለተኛ ነገሩን በአወንታዊ መልኩ፣ በተለይ ከህዝቡ የመጣውን ጥቄ በአወንታዊ መልኩ ማየት ጥሩ ነው  ብየ አስባለሁ፡፡” ነው ያሉት፡፡

ከአማራ ክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተጨማሪ አስተያየት ለማካተት ያደረግሁት ጥረት ስልክ ማንሳት ባለመቻላቸው አልተሳካም፡፡
በአማራ ክልል ከአንድ ዓመት በፊት የተቀሰቀሰው የፀጥታ መደፍረስ በክልሉ ሰብአዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳቶችን አድርሷል፡፡
በባሕር ዳር በተካሄደው የሰላም ጉባኤ፣ ከፍተኛ የመከላከያ ሰራዊት አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሐይማኖት አባቶች የፌደራል መንግስት አመራሮች  የአማራ ክልል የዞንና የክልል ባለስልጣናት ተሳትፈውበታል፡፡

ሙሉ ዝግጅቱን የድምፅ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።

 

ዓለምነው መኮንን
ነጋሽ መሀመድ
ፀሐይ ጫኔ