1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መቀሌን ጨምሮ የትግራይ ከተሞች በአሸንዳ ደምቀዋል

ሐሙስ፣ ነሐሴ 16 2016

መቐለ በአሸንዳ ደምቃለች። ሺዎች የሚቆጠር እንግዳ ለአሸንዳ በዓል ወደ መቐለ ገብቷል። አሸንዳ ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀን በድምቀት የሚከበር ሲሆን ከባህልዊ እና ሃይማኖታዊ ትውፊቱ በዘለለ ኢኮኖሚያዊ ትርጉሙም ትልቅ ሆኗል።

https://p.dw.com/p/4jnQH
Äthiopien | Ashenda Fest in Tigray
ምስል Million Hailesillasie/DW

የአሸንዳ በዓል በትግራይ ክልል በድምቀት መከበር ጀመረ

መቐለ በአሸንዳ ደምቃለች። ሺዎች የሚቆጠር እንግዳ ለአሸንዳ በዓል ወደ መቐለ ገብቷል። አሸንዳ ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀን በድምቀት የሚከበር ሲሆን ከባህልዊ እና ሃይማኖታዊ ትውፊቱ በዘለለ ኢኮኖሚያዊ ትርጉሙም ትልቅ ሆኗል።

የአሸንዳ በዓል አከባበር በመቀሌ

የተሳተፉበት ያሉ፣ ከጦርነቱ በኃላ መቐለ ጨምሮ ሌሎች ከተሞች ያነቃቃው የአሸንዳ በዓል አካባቢ ከዛሬ ጀምሮ በመቐለ በድምቀት መከበር ጀምሯል። ከተማዋ በባህላዊ ትርኢቶች፣ የሴቶች ጭፈራ እና ዘፈን፣ ጥበብ ደምቃለች።

የአሸንዳ ወይም የሻደይ በአል አከባበር

በዚህ በየዓመቱ ከነሐሴ 16 ማለትም ፆመ ፍልሰታ መጠናቀቅ በኃላ ለተከታታይ ሶስት ቀን የሚከበር በዓል፥ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የመጡ እንግዶችም ታደመውበታል።

የአሸንዳ በዓል በትግራይ በድምቀት እየተከበረ ነው
የተሳተፉበት ያሉ፣ ከጦርነቱ በኃላ መቐለ ጨምሮ ሌሎች ከተሞች ያነቃቃው የአሸንዳ በዓል አካባቢ ከዛሬ ጀምሮ በመቐለ በድምቀት መከበር ጀምሯል። ከተማዋ በባህላዊ ትርኢቶች፣ የሴቶች ጭፈራ እና ዘፈን፣ ጥበብ ደምቃለች።ምስል Million Hailesillasie/DW

እየደመቁ የመጡት የልጃገረዶች እና ሴቶች በዓላት

በከተማው ካለው ደማቅ ድባባ፣ በሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ የሚከፈልባቸው የሙዚቃ ድግሶች እና ሌሎች እንቅስቃሴዎች ውጪ የሆነ ሁነት ደግሞ በሌላው የመቐለ ክፍል መመልከት ይቻላል። በመቐለ ሰብዓ ካሬ በተባለው የተፈናቃይ መጠልያ ያሉ ሴቶች በዓሉ እንደሌሎች በቤታቸው እያከበሩ አይደሉም።

 

ሁለት መልክ የያዘው በዓል በአብዛኛው የትግራይ ከተሞች መከበር ጀምሯል።

ታምራት ዲንሳ 

ሚሊዮን ኃይለስላሴ

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር