መስጊዶች በሮቻቸዉን ከፍተዉ ዋሉ
ማክሰኞ፣ መስከረም 28 2000ማስታወቂያ
በጀርመን ባለዉ የእስልምና ምክር ቤት የዝርዝር ማወቅያ ሰንጠረዥ መሰረት 3.3 ሚሊዮን የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች በጀርመን ይኖራሉ። 164 ያህል መስጊዶች እና 2500 ያህል አዳራሽ መሰል የጸሎት ማድረግያ ቦታዎች ይገኛሉ። በኖርድ ራይ ዊስት ፋልያ ግዛት በቁጥር በርከት ያለ ማለት 25 ያህል መስጊድ እንዳለ እና በርካታ የሃይማኖቱ ተከታዮች የሚኖሩበት የጀርመን ግዛት እንደሆነም ተገልጾአል። በጀርመን ጥንታዊ የተባለዉ መስጊድ በ Baden-Wüttemberg ግዛት Schwetzingen እንደ አ.አ 1783 የተገነባ ሲሆን 225 አመቱን የያዘዉ መስጊድም ነዉ ምንም እንኳ የመስጊድ ግንባታ በጀርመን ጥንታዊነት ቢኖረዉም በአሁኑ ወቅት በጀርመን በሚገኙ ታላልቅ ከተሞች መስጊድን ለመገንባት የተነሳዉ ሃሳብ አከራኪ ሲሆን ይታያል።
በጀርመን የሚገኙ መስጊዶች ለጎብኝዎች በሮቻቸዉን ከፍተዉ መዋላቸዉ ዛሪ የባህል መድረካችን በዋናነት የሚዳስሰዉ ርእስ ሲሆን በተጨማሪ በዶቸ ቬለ ራድዮ ጣብያ ሰራተኞች የሆኑ ከተለያዩ አገሮች የመጡ የስልምና ሃይማኖት ተከታዮች በጀርመን ስላለዉ መንፈሳዊ ህይወታቸዉ ያጫዉቱናል መልካም ቆይታ