1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሕወሓት ብቻውን ትግራይን ወክሎ መደራደር የለበትም መባሉ

ሰኞ፣ ሰኔ 20 2014

በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ሶስት የፖለቲካ ፖርቲዎች ሕወሓት በብቸኝነት ትግራይን ወክሎ መደራደር የለበትም አሉ። በሂደት ላይ ባለው ድርድር ትግራይ ሁሉን አካታች በሆነ የድርድር አካል መወከል እንደሚገባ ባይቶና፣ ሳልሳይ ወያነ ትግራይና የትግራይ ነፃነት ፖርቲ አስታውቀዋል።

https://p.dw.com/p/4DIVA
Äthiopien Tigray-Provinz Mekele
ምስል EDUARDO SOTERAS/AFP

ሕወሃት ብቻውን የትግራይ ክልልን ወክሎ እንዳይደራደር የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠየቁ

በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ሶስት የፖለቲካ ፖርቲዎች ሕወሓት በብቸኝነት ትግራይን ወክሎ መደራደር የለበትም አሉ። በሂደት ላይ ባለው ድርድር ትግራይ ሁሉን አካታች በሆነ የድርድር አካል መወከል እንደሚገባ ባይቶና፣ ሳልሳይ ወያነ ትግራይና የትግራይ ነፃነት ፖርቲ  አስታውቀዋል።
ሁለት ዓመት ሊሞላው ጥቂት ከቀረው ደም አፋሳሽ ጦርነት በኋላ፤ ግጭቱን በድርድር ለመፍታት ከኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት ከሚመራው የትግራይ ክልል መንግስት በኩል ፍላጎትና ዝግጁነት ስለመኖሩ እየተገለፀ ባለበት በዚህ ወቅት በትግራይ ያሉ የፖለቲካ ኃይሎች፥ ሂደት ላይ አለ ባሉት ድርድር ትግራይ በብቸኝነት በህወሓት መወከል የለባትም ሲሉ ገልፀዋል።
ባይቶና፣ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ እና የትግራይ ነፃነት ፖርቲ በጋራ ለአለማቀፉ ማሕበረሰብ በአጠቃለይ እንዲሁም ለአደራዳሪ አካላት ባሰራጩት መግለጫ ግጭቱን ለመፍታት ከትግራይ በኩል ህወሓትን ብቻ ማዕከል ያደረገ ድርድር ማድረግ ስህተት ነው ብለዋል።

ሚሊዮን ኃይለስላሴ

ታምራት ዲንሳ

አዜብ ታደሰ