1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ተሻሽሎ የፀደቀው አዋጅ 

ሐሙስ፣ ሐምሌ 1 2013

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ትናንት ያፀደቀው አዋጅ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አሁን እየቀረቡ ካሉ የሕዝብ ፍላጎቶችና ጥያቄዎች አንፃር፣ በሕገ መንግሥቱ የተሰጡትን ተልዕኮዎች በቀልጣፋና በውጤታማ መንገድ ለመፈጸም በሚያስችለው ሁኔታ ላይ ባለመገኘቱ የተሻሻለ ነው ተብሏል።

https://p.dw.com/p/3wDkc
Äthiopien Logo Parlament  FDRE

ተሻሽሎ የፀደቀው አዋጅ 

በሁለት ክልሎች ወይም በፌዴራልና በክልሎች መካከል የሚነሱ አለመግባባቶችን ለመፍታት፣ ክልሎች ችግሩ እንዲፈታ ካልጠየቁ ፣ሆኖም ችግሩ ከቀጠለ የፌደሬሽን ምክር ቤት በራሱ ተነሳሽነት መፍትሔ እንዲፈልግ የሚፈቅድ የተሻሻለ አዋጅ ፀደቀ። ነባሩ አዋጅ ሁለቱ ወገኖች ካልተስማሙ በአንድ ወይም ሁለቱ ወገኖች በሚቀርብ ጥያቄ ምክር ቤቱ ለጉዳዩ መፍትሔ እንዲሰጥ ቢደነግግም በተግባር የመፍትሔ እርምጃ ሳይወስድ ቆይቷል።የሕዝብ ተወካዮች ምክር ትናንት ያፀደቀው አዋጅ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አሁን እየቀረቡ ካሉ የሕዝብ ፍላጎቶችና ጥያቄዎች አንፃር፣ በሕገ መንግሥቱ የተሰጡትን ተልዕኮዎች በቀልጣፋና በውጤታማ መንገድ ለመፈጸም በሚያስችለው ሁኔታ ላይ ባለመገኘቱ የተሻሻለ ነው ተብሏል።በማሻሻያ አዋጁ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ የሕግ ባለሙያ መንግሥት በቅርብ ጊዜ ሕገ መንግሥታዊ አተረጓጎም ሥርዓቱን የሚመለከተውን የሕገ መንግሥት ክፍል የማሻሻል ውጥን እንደሌለው አመላካች ነው ብለዋል።
ሰሎሞን ሙጬ 
ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ