1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለጋሞ የአደጋ ሰለባ ቤተሰቦች የሚደረገው የርዳታ ሁኔታ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 18 2016

ደቡብ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኘው ጎፋ ዞን በተከሰተው የመሬት ናዳ ክፉኛ ለተጎዱ ዜጎች መሠረታዊ የሰብአዊ ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ለዶቼ ቬለ ገለፁ።

https://p.dw.com/p/4ijNt
Äthiopien Rettungseinsatz und humanitäre Hilfe in der Gofa-Zone
ምስል Gofa Zone Government Communication Affairs Department

በጎፋ የአደጋ ሰለባ ቤተሰቦች የሚደረገው ርዳታ እንዲጠናከር ተጠየቀ

ለመሬት ናዳ ሰለባዎች እየተደረገ ያለው ድጋፍ

 

ደቡብ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኘው ጎፋ ዞን በተከሰተው የመሬት ናዳ ክፉኛ ለተጎዱ ዜጎች መሠረታዊ የሰብአዊ ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ለዶቼ ቬለ ገለፁ።

እነዚህ የሰብአዊ ድጋፍ ሰጪ ተቋማት፣ የሟቾች ቁጥር በየ ሰዓቱ እያሻቀበ ከሚገኘው የተፈጥሮ አደጋ የተረፉትን ሰዎች ለማብላት፣ ለማልበስና ከክረምቱ ዝናብ ለመታደግ፣ አስፈላጊ ያሏቸውን ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች እያቀረቡ መሆኑን አስታውቀዋል።

በጎፋ ዞን በደረሰ የመሬት መንሸራተት ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ወደ 55 ማሻቀቡን ባለሥልጣናት ተናገሩ

የባለፈው ሳምንት ማብቂያ እሑድ ሐምሌ 14 ቀን እና የዚህኛው ሳምንት መጀመርያ ሰኞ ዕለት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ በጎፋ ዞን የደረሱት አሰቃቂ ጉዳትም ያስከተሉት የመሬት መንሸራተት አደጋዎች፣ የሟቾች ቁጥር በየሰዓቱ እየጨመረ ቢሆንም እስካሁን 230 የሚሆኑ ዜጎችን እንደገደሉ ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ።

በኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን ከፍተኛ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ አታለል ይባዝን ዛሬ ሐሙስ ለዶቼ ቬለ

እንዳሉት፣ ከአደጋው ቢተርፉም ተፈናቅለው ለፈተና ለተዳረጉት ሰብዓዊ ድጋፍ እየተደረገ ነው።

«በጎፋ ወረዳው የመሬት መንሸራተት አደጋ ከ2 ሺህ በላይ ሰዎች የአስቸኳይ ግዜ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል።»

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በዚሁ ስፍራ የደረሰው የተፈጥሮ አደጋ ያስከተለውን ሞት እና የጉዳት መጠን የሚመጣጠን የምግብ እና መሠረታዊ የሰብአዊ ድጋፍ በተቀናጀ ሁኔታ እና በአፋጣኝ እንዲቀርብ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል።

የጎፋ የመሬት መንሸራተት አደጋ በርካቶችን ለህልፈት ዳርጋል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በዚሁ ስፍራ የደረሰው የተፈጥሮ አደጋ ያስከተለውን ሞት እና የጉዳት መጠን የሚመጣጠን የምግብ እና መሠረታዊ የሰብአዊ ድጋፍ በተቀናጀ ሁኔታ እና በአፋጣኝ እንዲቀርብ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል።ምስል Gofa Zone Government Communication Affairs Department

ይህ የደረሰው አስከፊ ናዳ ያስከተለው ችግር ካደረሰው ሞት ባለፈ የዜጌችን መኖሪያዎች እንዳልነበር አድርጓል፣ መተዳደሪያዎቻቸውንም በብርቱ አውድሟል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች እስካሁን እየተደረገ ያለው ድጋፍ የሚያበረታታ እንደሆነም ገልጿል። በኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን ከፍተኛ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያው አቶ አታለል ይባዝን ወቅቱ ክረምት እንደመሆኑ መጠነኛ እና ከፍተኛ ዝናብ ሊኖር ስለሚችል፣ ያንንም ታሳቢ ያደረገ የቁሳቁስ እርዳታ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

የጎፋው ዘግናኝ የተፈጥሮ አደጋ

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አደጋው ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ አስፈላጊ የሆኑ ያላቸውን ድጋፎች እያደረገ መሆኑን፣ የተቋሙ ሠራተኞች እና በጎ ፈቃደኞች ምግብ፣ ብርድ ልብስ፣ መጠለያ እና የንፅህና ቁሶችን ጨምሮ ወሳኝ የተባሉ እርዳታዎችን እያደረሰ እንደሚገኝ፣ ጥረቱንም ለማስፋት ቁርጠኞ መሆኑን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

የሰብአዊ ርዳታ ርክክብ ለጎፋ የመሬት መንሸራተት ተ,ጎጂዎች
ብሔራዊ አደጋ ሥጋት የአካባቢው ሕዝብ ሕይወትን ለማዳን ሲል ወደ ሞት መሄዱ የሚደነቅ ኢትዮጵያዊነት ነው ሲል ትብብሩና ድጋፉ እንዲቀጥል ጠይቋልምስል Gofa Zone Government Communication Affairs Department

ብሔራዊ አደጋ ሥጋት የአካባቢው ሕዝብ ሕይወትን ለማዳን ሲል ወደ ሞት መሄዱ የሚደነቅ ኢትዮጵያዊነት ነው ሲል ትብብሩና ድጋፉ እንዲቀጥል ጠይቋል።

የጎፋ ነዋሪዎች የምግብ ርዳታ ጥያቄ

ይህ የተፈጥሮ አደጋ ከተከሰተበት ዕለት ጀምሮ ግለሰቦች፣ ልዩ ልዩ ተቋማት፣ የመንግሥት መዋቅሮች ሀዘናቸውን ከመግለጽ ባለፈ የጉልበት፣ የቁሳቁስ እና የሀብት ድጋፍ እያደረጉ ይገኛሉ። የጎረቤት ሀገራት እና የአፍሪካ ሕብረት መሪዎችም በደረሰው አደጋ ማዘናቸውን ሲገልፁ ተስተውሏል።

ሰለሞን ሙጬ

ታምራት ዲንሳ 

እሸቴ በቀለ