ለጀርመን አማራጭ ፓርቲ አወዛጋቢ አስተያየት
ሰኞ፣ ግንቦት 22 2008ማስታወቂያ
የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አሌግዛንደር ጋውላንድ የባየር ሙንሽን እና የብሔራዊ ቡድን ተከላካይ ተጫዋች የሆነውን ጄሮም ቡዋቴንግን እና ሌሎች የብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾችን አስመልክተው የሰነዘሩት « ለተጫዋችነት እሺ፣ ለጎረቤትነት ግን አልፈልግም» የሚለው አስተያየት በብዙ ጀርመናውያን፣ በባለስልጣናትም ዘንድ ቁጣ ቀስቅሶዋል። የአማራጭ ለጀርመን ፓርቲ ምክትል ሊቀ-መንበር ከጋናዊ አባት እና ጀርመናዊት እናት በርሊን ውስጥ የተወለደው ቡዋቴንግ ታዋቂ ቢሆንም 'መጤ' ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
እሸቴ በቀለ
አርያም ተክሌ