ግጭቱ ከመሬት ይገባኛል ጋር የተያያዘ ነው ተብሏል
ዓርብ፣ ታኅሣሥ 13 2010ማስታወቂያ
በደቡብ ክልል የሚገኙ የሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ አባል ለዶይቼ ቬሌ እንደተናገሩት ከትላንት በስቲያ ምሽት ረቡዕ ጭምር ግጭት ነበር። በዚህም ሰዎች መሞታቸውን ተናግረዋል። የአማሮ ወረዳ አስተዳዳሪ በበኩላቸው ከመሬት ይገባኛል ጋር በተያያዘ ግጭት እንደነበር ያምናሉ። ሁኔታው እየተረጋጋ እንደሆነ ቢገልጹም ዘላቂ ሰላም ተፈጥሯል ብሎ መናገር እንደማይቻል አመልክተዋል። የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ ሁለቱንም ወገኖች አነጋግሯል። ዝርዝር ዘገባውን የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን ያድምጡ።
ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
ሸዋዬ ለገሠ